እናት ታታ ታከል አረፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​​ደጓ እናት ታታ ታከል ባደረባቸው የጤና እክል ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ትላንት ማምሻውን በክብር አርፈዋል።

በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ አሻራቸውን ጥለው የሚያልፉ ብርቅዬ ሰዎች ሁሌም በክብር ይነሳሉ። በታዋቂው የፊልም ባለሙያ ጋሽ ኃይሌ ገሪማ “ጤዛ” ፊልም ላይ የአንበርብር እናት ሆነው ባሳዩት ድንቅ የትወና ብቃት በብዙዎቻችን ልብ ህያው ስፍራ አግኝተዋል።

በፊልሙ ላይ ባሳዩት ተፈጥሯዊና የእናትነት ስሜት በኢትዮጵያ ሲኒማ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ አሻራ ጥለው ያለፉት ታታ በህይወት ዘመናቸው ባሳዩት ደግነትና ቅንነት በብዙዎች ዘንድ ዘላለማዊ ፍቅርና ክብርን አትርፈዋል።

ነፍስ ይማር 🕯🕯

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: