የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ አውሮፕላን ተረከበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከካናዳው ታዋቂ አውሮፕላን አምራች ኩባንያ ‘ዴ ሃቪላንድ ካናዳ’ ለመረከብ ካቀዳቸው ሁለት ዘመናዊ የ’ዲኤችሲ-6 ትዊን ኦተር ክላሲክ 300-ጂ’ አውሮፕላኖች መካከል የመጀመሪያውን በዛሬው ዕለት በይፋ ተረክቧል።

ይህ አዲስና ልዩ የሆነ አውሮፕላን በተለይም የሀገር ውስጥና የቀጣናዊ በረራ አገልግሎቶችን ይበልጥ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ ትልቅ አቅም ይዞ የመጣ መሆኑ ተገልጿል።

​አውሮፕላኑ ለመደበኛ የመንገደኞች ትራንስፖርት ከሚሰጠው ጥቅም ባሻገር፣ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ዘርፍ መነቃቃት፣ ለአየር ላይ የቅኝትና የጥናት ሥራዎች እንዲሁም ለአስቸኳይ የአየር አምቡላንስ አገልግሎት ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚኖረው አየር መንገዱ አስታውቋል።

አየር መንገዱ እያደገ የመጣውን የተለያየ የገበያ ፍላጎት በብቃትና በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላት ለሚያደርገው ጉዞ ይህ አዲስ እምርታ ተደራሽነቱን ይበልጥ እንደሚያሰፋው ይጠበቃል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2