አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የ10 ዓመት ጎልደን ቪዛ ተሸለመ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ታዋቂው የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ)፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት የ10 ዓመት የ”ጎልደን ቪዛ” (Golden Visa) ተሸላሚ ሆነ።

​አቤል ይህንን የረዥም ጊዜ የመኖሪያ ፈቃድ ያገኘው በይዘት ፈጠራ (Content Creation) ዘርፍ ባበረከተው አስተዋጽኦ ነው። ሽልማቱን ተከትሎ ባስተላለፈው መልእክት፣ ይህ ዕድል ለወደፊት ለሚያቅዳቸው ዓለም አቀፍ የጉዞ ዶክመንተሪዎች እና ሌሎች የሥራ ዘርፎች ትልቅ መነሳሻ እንደሚሆነው ገልጿል።

​የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥት በተለያዩ የሙያ መስኮች የላቀ ውጤት ላመጡ ግለሰቦች የሚሰጠው ይህ ጎልደን ቪዛ፣ በኢሚግሬሽን ሥርዓቱ ውስጥ ትልቅ ክብር የሚሰጠው የቪዛ ዓይነት ነው። አቤል በምስጋና መልእክቱ፣ ይህ ስኬት ከጀርባው ሆነው ለሚደግፉት ተከታዮቹ እና ለአምላኩ የሚገባ መሆኑን ጠቅሷል።

​አቤል ብርሃኑ በኢትዮጵያ የዲጂታል ሚዲያ እና የይዘት ፈጠራ ዘርፍ ታዋቂ ከሆኑ ግለሰቦች አንዱ ሲሆን፣ በጉዞ እና በዶክመንተሪ ስራዎቹ በርካታ ተከታዮችን ማፍራት ችሏል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: