የኢዜማ የምርጫ 2018 86 መቀመጫዎችን ማሸነፉን አስታወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2018 ሀገር አቀፍ ምርጫ ይፋዊ ውጤትን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በምርጫው ያገኘውን ውጤት በመግለጽ ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ጥሪ አቅርቧል። ፓርቲው በምርጫው በድምሩ 86 መቀመጫዎችን በማሸነፍ አጠናቋል።

​የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ትላንት ባወጣው ይፋዊ ውጤት መሠረት፣ ኢዜማ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተወዳደረባቸውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13 ወንበሮች እንዲሁም 73 የክልልና የከተማ ምክር ቤት ወንበሮችን በማሸነፍ አጠቃላይ 86 መቀመጫዎችን ይዟል።

​ፓርቲው በሰጠው መግለጫ፣ ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን በመጥቀስ ለዕጩዎቹ፣ ለአባላቱ እና ለደጋፊዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፏል። ኢዜማ በውጤቱ በመደሰት ብቻ ሳይወሰን፣ የቀጣዮቹን ዓመታት የሥራ አቅጣጫ በግልጽ አስቀምጧል።

​ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ያስተላለፈው ኢዜማ፤ ገዢው ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን በመገንባት፣ ፍትሐዊ የፖለቲካ ምህዳርን በመፍጠር፣ አማራጭ ሀሳቦችን በመቀበል እና ትችቶችን በሆደ ሰፊነት በማስተናገድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርቧል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2