መርጌታ ነኝ በማለት 625 ሺህ ብር ያጭበረበረው ግለሰብ በምስራቅ ጎጃም በቁጥጥር ስር ዋለ።

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ተጠርጣሪ አብርሀም ሰርኬ መርጌታ ነኝ በሚል የሐሰት ስም አቶ ደነቀው ሙሉቀን ከተባለው በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በዳንሻ ከተማ አስተዳደር በሆቴል ስራ ከተሰማራ ግለሰብ 625ሺህ ብር አታሎ መውሰዱን የሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ኢንስፔክተር በድሉ መልሰው ተናግረዋል።

ወንጀሉን የፈፀመው ግለሰብ እቁብ እንዲደርስህ አደርጋለው በማለት ከታህሳስ 2018ዓ.ም ጀምሮ ብሩን አታሎ መውሰዱ ተገልፆ በተጨማሪ ሦስት መቶ ሺህ ብር ካልጨመረክ ቤተሰብህን በሙሉ በመተት አጠፋብሐለው በማለት በተበዳይ ላይ አደገኛ የማጭበርበር ወንጀል ሲፈፅም መቆየቱ ተመላክቷል።

የዳንሻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የፍ/ቤት መያዥያ ትዕዛዝ በማውጣት ተጠርጣሪው በተገኘበት በቁጥጥር ስር እንዲውል በፃፈው የትብብር ደብዳቤ ከምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የመረጃ ክትትል ቡድን ጋር በመተባበር ግለሰቡ ሰኔ 15/2018 ዓ.ም በሉማሜ ከተማ አስተዳደር በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎል።

አቶ ደነቀው ሙሉቀን በደረሰበት የማታለል ወንጀል ምክንያት
ለከፍተኛ ስነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር ተጋልጦ በፀበል ቦታ እንደቆየ ተገልፆ ተጠርጣሪው በአሁን ሰዓት ምርመራ እየተደረገበት እንደሚገኝ ከሉማሜ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ያገኝነው መረጃ ያመላክታል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2