”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ ያሎት” ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የማሌዢያው ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም በኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ለብልጽግና ፓርቲ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፈው ዓመት በአዲስ አበባ ያደረጉትን ታሪካዊ ጉብኝት ያስታወሱ ሲሆን፣በወቅቱ በተደረጉት ውይይቶችና በተደረገላቸው ሞቅ ያለ አቀባበል እጅግ ተደስተው እንደነበር ገልጸዋል።

​በውይይቶቻቸው ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ተመሳሳይ አመለካከት እንዳላቸው የተረዱ ሲሆን በደቡብ ንፍቀ ክበብ አገራት የጋራ እድሎች ዙሪያ አውርተናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ማሌዢያ ከአፍሪካ አህጉር ጋር ለምታደርገው ግንኙነት ትልቅ መነሻና የላቀ ሚና ያላት አገር መሆኑን የጠቀሱት አንዋር ባለፈው ዓመት የተጀመሩ የሁለትዮሽ ስምምነቶችንና ሥራዎችን ይበልጥ ለማጠናከርና ወደፊት ለማስቀጠል በጉጉት እንደሚጠብቁ አስታውቀዋል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1