የጉዞ ማስታወሻ(ክፍል 2) ይጠብቁኝ
#Ethiopia | የ2026ቱን የአለም ዋንጫን በአካል ተገኝተው እንዲዘግቡ ዕድል ከተሠጣቸውና ከመላው ዓለም ከተውጣጡ 16ሺ የስፖርት ጋዜጠኞች አንዱ ሆኜ የኢትዮጵያን ምድር ለቅቄ በካናዳ ከመሸኩ ወይም እንደ ቀልድ ከሀገሬ ከወጣሁ ነገ(ረቡዕ)15ኛ ቀኔን እደፍናለሁ፤ ዕድሜ የቀጠልኩባቸውን፣አዳዲስ ተዓምራትን ያየሁባቸውን እነዛ ውብና ታሪካዊ ቀናቶችንም 15 ሻማዎችን ለኩሼም አከብራለሁ።
ፊፋ በሠጠኝ ዕድል መሠረት በ BMO Field ቶሮንቶ ስታዲየም ከዛሬ ጋር አራት ጨዋታዎችን የመታደም ዕድል አግኝቻለሁ፤
የስምንት ሀገራት ብ/ቡድኖችንና የአርሰናሉ ካይ ሀቨርስ፣የሊቨርፑሉ ፍሎራን ዊርዝ፣ የባየር ሙኒኩን ጆሹዋ ኪሚችን፣የባየር ሙኒኩን ማኑዌል ኑየርን፣የስቱትጋርቱን ዴኒስ ኡንዳቭ፣የማን ዩናይትዱን ኮከብ አማዱ ዲያሎ፣የሳውዲው አል-አህሊን ፍራንክ ኬሲን፣የመሳሠሉት ከዋክብትን ይሄ ታሪካዊ የዓለም ዋንጫ አሳይቶኛል፤ወደ አሜሪካ ተሻግሬም የፍፃሜውን ጨመሮ የተለያዩ ጨዋታዎችን የመታደምም ዕድል ስላለኝ የተጫዋቾቹም የጨዋታዎቹ ቁጥርም ከፍ ማለቱም ግድ ነው።
ዛሬም ፓናማ ከ ክሮኤሽያ በቶሮንቶ ስታዲየም የሚያደርጉትን ጨዋታ እንድመለከት ተጋብዣለሁ ብቻ ሳይሆን በክብር የምቀመጥበትና የምከታተልበት ብሎክ ቁጥርም ተሠጥቶኝ የውድድሩን ሠዓት በመጠባበቅ ላይ እገኛለሁ።
የሜዳ ውስጡ በተለያየ መንገድ የሚታይ ቢሆንም ከሜዳ ውጪ(Off the Pitch) ያለውን አስገራሚ ነገር በክፍል አንድ የጉዞ ማስታወሻዬ በወፍ በረር አጋርቼያችሁ እንደነበር የሚታወስ ነው፤አሁን ደግሞ ሌሎች ትዝብቴንና አስገራሚ ገጠመኞችን ምሽት 1:30 ላይ ላጋራችሁ፣መሠናዶዬን አጠናቅቄያለሁ፤ ጊዜአችሁን እንድታውሱኝሜ በአክብሮት እጠይቃለሁ።
♦️ምሽት 1:30 ላይ በማቀርበው ሁለተኛው ክፍል የጉዞ ማስታወሻዬ በካናዳ ኒያግራ ፎልስ አካባቢ ስላገኘኋት 6 ወንበርና ሁለት መፅሐፍ ቅዲስ ብቻ ስላላት ዕድሜና ታሪክ ጠገቧ የካናዳ በጣም ትንሿ ቤተክርስቲያን የምላችሁ ይኖራል ጠብቁኝ፤
በኒያግራ ፎልስ ያገኘኋት ይህቺው የካናዳ ምንአልባትም የዓለም ትንሿ ቤተክርስቲያን ስድስት ሠዎችን የሚያስተናግዱ ስድስት የእንጨት ወንበሮችና ሁለት መፅሐፍ ቅዱሶችን ብቻ ብቻ በውስጧ ሸሽጋ ብትይዝም በትንሿ ቤተክርስቲያን ውስጥ እጅግ በጣም ግዙፍ ፀጥታ፣ተስፋ፣ዕምነት ይታፈስበታልና በዚህች ትንሽ ግን በታሪኳ ግዙፍ በሆነችው ቤተክርስቲያን በአካል ተገኝቼ የታዘብኩትን አስገራሚ ታሪክ አጋራችኋለሁ
♦️ሌላው እጄን በግርምት ያስጫነው Floral Clock የሚባለው የካናዳዊያን ትልቁና ባለሪከርዱ ሠዓት ነው
🙏🙏ምስጋና ለልበ ቀናው የተዋጣለት አስጎብኚዬ፣ታሪክን ፈትፍቶ ለሚያጎርሠው Tour Guide ካሌብ እና እኔ ምግብ ሳይሆን ለተከታዮችህ የምታጋራው ታሪክ ነው የምመግብህ ብሎ ዕድሜ ዘመኔን ስዘረዝረው የምኖረው ታሪክን ከኒያግራ ፎልስ አፍሼ እንድመለስ ገንዘቡን ከስክሶ ላመቻቸልኝ የህግ ባለሙያው፣ለኢትዮጵያዊያን ችግር ፈጥኖ ደራሹና በካናዳ የሀገር መመኪያ ለሆነው ተክለሚካኤል አበበ ይግባና ተዓምረኛውንና አስገራሚውን ትልቁን የካናዳ ሠዓት(Floral Clock)ብዙ የማጋራችሁ ነገር አለ ምሽት 1:30 ጠብቁኝ።🙏🙏
♦️ምሽት 1:30 የማጋራችሁ የካናዳዊያን ትልቁ ሠዓት Floral Clock እንደ ማንኛውም ሠዓት ጊዜን ብቻ የማይቆጥር ሠዓት ነው፣በብረት ሠከንዶች ፋንታ አበቦች የሚናገሩበት ሠዓት ነው፣በደቂቃዎች ፋንታ ነፍስን የሚያውድ የተፈጥሮ አበቦች ሽታን የሚያመነጭ ሠዓት ነው፣በዚህ ቦታ ጊዜ አይሮጥም፤ይልቁንም አበቦችን የሚያበቅል ጊዜን የሚያሳምር ጉደኛ ሠዓት ነው፣
♦️በካናዳ ቶሮንቶ ቆይታዬ ከሜዳ ውጪ(Off the Pitch)የታዘብኳቸውን እነዚህንና ሌሎች ካናዳ በጉያዋ ሸሽጋ የያዘቻቸውን ምስጢሮች አንዳችም ሳልሠስት አካፍላችኋለሁ ምሽት 1:00 ጠብቁኝ።
✍️ጋዜጠኛ ይሴሀቅ በላይ
(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)ከካናዳ ቶሮንቶ


Source: GetuTemesgen









No comments yet.