ከማረሚያ ቤት በወጣ በ3ኛ ቀን የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ
ዳዊት በላቸው የተባለው ተከሳሽ ከዚህ ቀደም የቅሚያ ወንጀሉን የፈፀመው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አረንጓዴ ሰፈር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ/ም ነበር።
ግለሰቡ የዋጋ ግምቱ 25 ሺህ ብር የሚያወጣ ሳምሰንግ M 32 ሞባይል ከግል ተበዳይ ላይ ቀምቶ ለማምለጥ ሲሞክር በፖሊስ አባላትና በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፈንጅ ተይዞ አስፈላጊውን ምርመራ ከተጣራበት በኋላ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶበት ጉዳዩን የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ወንጀል ችሎት በ3 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፎበት በማረሚያ ቤት መቆየቱን በክፍለ ከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ የቤተል አካባቢ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
የ3ዓመት የእስር ጊዜውን ጨርሶ ከማረሚያ ቤት የወጣውና ያልታረመው ይህ ግለሰብ በወጣ በ3ኛው ቀን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ቤተል አካባቢ ከሚገኝ አንድ አፖርታማ ገብቶ 19 ሺህ ብር የሚገመቱ የተለያዩ ጫማዎችን ሰርቆ ለማምለጥ ሲሞክር ስራ ላይ በነበሩ የወንጀል መከላከል የፖሊስ አባላትና በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፈንጅ መያዙን የቤተል አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
የተሰረቁት ንብረቶች በኤግዚቢት ተይዘው በግለሰቡ ላይ አስፈላጊው ምርመራ ከተጣራበት በኋላ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶበታል፤ ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ፈጣን ወንጀል ችሎት ተከሳሹን ያስተምራል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በማለት ሰኔ16 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በፈፀመው ደጋጋሚ የወንጀል ድርጊት በ4 አመት ከ5 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ እንዳስተላለፈበት ፖሊስ ጠቅሷል፡፡
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.