አቤል ብርሃኑ ከዩኤኢ የ10 ዓመት የጎልደን ቪዛ ተበረከተለት!ታዋቂው የቪዲዮ ይዘት አዘጋጅ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) ከተባ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አቤል ብርሃኑ ከዩኤኢ የ10 ዓመት የጎልደን ቪዛ ተበረከተለት!
ታዋቂው የቪዲዮ ይዘት አዘጋጅ አቤል ብርሃኑ (የወይኗ ልጅ) ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የ10 ዓመት የጎልደን ቪዛ (Golden Visa) ተበርክቶለታል።
በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የረጅም ጊዜ መኖሪያ ፍቃድ ማግኘት፣ በተለይም ደግሞ ሙሉ መብትን የሚያጎናጽፈውን የ10 ዓመት የጎልደን ቪዛ ባለቤት መሆን በአለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ታዋቂ እና ከባድ ከሚባሉ የነዋሪነት እውቅናዎች መካከል አንዱ ነው።
ይህ ታላቅ እድል አብዛኛውን ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ 2 ሚሊዮን ድርሃም ወይም በግምት ከ95 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በላይ ኢንቨስት ላደረጉ ትልልቅ ባለሀብቶች፣ በከፍተኛ የትምህርት ደረጃቸው እና ማህበራዊ አቅማቸው የወር ገቢያቸው ከ30 ሺህ ድርሃም በላይ ለሆኑ ባለሙያዎች፣ ልዩ ተሰጥኦ ላላቸው ግለሰቦች፣ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እንዲሁም ለሰብአዊ መብት እና ለበጎ አድራጎት ሰራተኞች የሚሰጥ ልዩ ስጦታ ነው።
ይሁን እንጂ ስኬታማውና በብዙ ሚሊዮኖች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ኢትዮጵያዊው የዲጂታል ይዘት አዘጋጅ አቤል ብርሃኑ፤ ይህንን ታላቅ ዕድል በማህበራዊ ሚዲያ ባለው ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና በፈጠራ ስራ አቅራቢነት ዘርፍ ከኤምሬትስ መንግስት ለመቀበል በቅቷል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2