በደቡብ አፍሪካ የጸረ ስደተኛ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ስደተኞች ሃገራቸውን ለቀው እንዲወጡ እስከ ሰኔ 30 ድረስ የጊዜ ገደብ ማስቀመጣቸውን ተከትሎ የሃገሪቱ ፖሊስ የደህንነት ስራዎቹን አጠናክሮ ለመቀጠል እንዳሰበ ተናግሯል።
የሃገሪቱ ጊዜያዊ የጸጥታ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መሰረት፤ ተጨማሪ የደህንነት አካላትን በሃገር አቀፍ ደረጃ ማሰማራቱን ገልጿል።
ሃገሪቱ ለሳምንታት በዘለቀ የመጤ ጠል እንቅስቃሴዎች ስትታመስ የሁለት ሰዎች ህይወት መጥፋቱንና የተለየዩ የአፍሪካ ሃገራት ከጥቃቱ ዜጎቻቸውን ለማሸሽ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር አልጀዚራ ዘግቧል።
የደህንነት ሚኒስትሩ የፖሊስ አገልግሎቱ በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች ተጠናክሮ መቀጠሉን እንዲሁም ማህበረሰቡንና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎችን ለመጠበቅ እንደሚሰሩ ገልጸው፤ሰላማዊ ከሆኑ ተግባራት ዉጪ ወንጀል ነክ ተግባራትን እንዲሁም የመብት ጥሰቶችን እንደማይታገሱ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስትር የጸጥታ ሃይሉ ስትራተጂያዊ የሆኑ አየር ማረፊያዎችን እንደሚጠብቅና የፖሊስ ሃይሉን በማንኛውም መልኩ ለማገዝ ዝግጁ እንደሆነ ተናግረዋል።
ሃናን ሸምሱ
Source: Yeneta Tube









No comments yet.