የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የታሪክ ቅርሶችና ሰነዶች እንዲሰበሰቡ ጥሪ አቀረበ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በየግለሰቦችና በየቤቱ ተበትነው የሚገኙ የታሪክ ቅርሶችን፣ ሰነዶችንና ጥንታዊ ቁሳቁሶችን በአንድ ማዕከል ሰብስቦ ለመጠበቅና ለምርምር ለማዋል አዲስ ጥሪ አቀረበ።

‎ዩኒቨርሲቲው “ኑ አብረን ታሪክ እንስራ፣ አብረን ታሪክ እንሰብስብ፣ አብረን ታሪክ እናስተላልፍ” በሚል መሪ ቃል ያወጣው ይህ ጥሪ፣ የሀገር ማንነትና የትውልድ መገናኛ ድልድይ የሆኑ ቅርሶች እንዳይጠፉና ለትውልድ እንዲሻገሩ ለማድረግ ያለመ ነው።

‎​የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር አስራት አጸደወይን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ የረጅም ዘመን ታሪክ ባለቤት ብትሆንም ብዙዎቹ የታሪክ ምስክር የሆኑ ቅርሶችና ሰነዶች በተለያዩ ግለሰቦች እጅ ተበታትነው ይገኛሉ። እነዚህ ቅርሶች በአግባቡ ባለመያዛቸው ምክንያት የመጥፋት ወይም የመበላሸት አደጋ የተጋረጠባቸው መሆኑን የጠቀሱት ዶክተር አስራት፣ ዩኒቨርሲቲው ይህንን የታሪክ ክፍተት ለመሙላት፣ ቅርሶችን ለመሰነድና ለምርምር አበርክቶ እንዲኖራቸው ለማድረግ የአርካይቭ፣ የቤተ መዛግብት እና የሙዚየም ማዕከላትን በአዲስ መልክ አደራጅቶ ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል።

‎​በመሆኑም በጥንታዊ የብራና ጽሁፎች፣ ደብዳቤዎች፣ የታዋቂ አርበኞችና መሪዎች የግል መገልገያ ቁሳቁሶች እንዲሁም ጥንታዊ ፎቶግራፎች በእጃቸው የሚገኙ ግለሰቦችና ቤተሰቦች እነዚህን ቅርሶች ለዩኒቨርሲቲው በስጦታ እንዲያበረክቱ ተጠይቋል።

‎ይህ ተግባር ቅርሶቹ በዘመናዊ መንገድ ተጠብቀው ለታሪክ ተመራማሪዎችና ለሚቀጥለው ትውልድ እንዲተላለፉ የሚያደርግ ሲሆን፣ በበጎ ተግባሩ ላይ የሚሳተፉ ዜጎችም ስማቸው በታሪክ መዝገብ ላይ በበጎነት እንደሚነሳ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ








Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: