የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት እና ምልጃው አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር፡፡ ታላላቆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅዱስ ፓውሎስንና ናትናኤል፣ በሌሊት ወደ ጌታ እየሔደ ይማር የነበረው ኒቆዲሞስንና በርካታ የኦሪት ምሁራንን ያስተማረው ታላቁ የኦሪት መምህር ገማልያል ዘንድ ጠንቅቆ የተማረ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5 ላይ ስለእርሱ በሰፊው ተጠቅሷል፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ የስሙ ትርጓሜ አክሊል እንዲሁም ውሃ የማያስገባ ብርሃን የሚያስገባ መደብ፣ ወደብ ለሆቴ ማለት ነው በሚል በቅዳሴ ማርያም አንድምታ ላይ ሰፍሮ እናገኘዋለን፡፡ በሕገ ወንጌል ክርስትና የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ነው፡፡ በኃይል በጸጋና በመንፈሳ ተሞልቶ የወንጌሉን ብስራት ይሰብክ እንደነበርም ይነገርለታል፡፡

ታላቁ ሰማዕት የመሲሁን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር፡፡ ኋላም የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለ6 ወራት በትጋት አገለግሎታል፡፡ ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲጠመቅ የተደረገውን ታላቅ ተአምር አይቶ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን ጠይቆ ወደ ጌታችን በመሔድ ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ተምሯል፡፡ ጌታም ከ72ቱ አርድእት አንዱ አድርጐ ለአገልግሎት ላከው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ባረገ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ሲባርክ እንደ ወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ቅስናን፣ ጵጵስናን ተሹሟል፡፡ በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ72ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት ምሥጢርም የተገለጠለት አልነበረም፡፡ በፍጹም ልቡም በእውቀት ወንጌልን ይሰብክ ነበር፡፡

በመንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ሰባት ዲያቆናትን ሲመረጡ እርሱ የ6ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበረ ክርስቲያን አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የሞላበት፣ የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረበት ቅዱስ እስጢፋኖስ ወንጌልን ቢያስፋፋ አይሁድ “ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው” ብለው በማመናቸውና በትምህርቱ ሊገዳደሩት ስላልቻሉ በተወለደበት ጥር 1 ቀን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፡፡ ሲወግሩትም ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ወልድን በአብ ቀኝ ተመለከተው፣ እንደ አምላኩ ለሚወግሩት ሰዎች “የሚያደርጉትን አያውቁም በማለት ይቅርታ ጠየቀ፡፡ ጌታችንም ሰማያዊ አክሊል ላከለት፡፡ ገዳማውያን ሰማዕቱን አብነት አድረገው በጸሎትና በጾም እየተጉ የሥጋ ፍላጎትን ድል ያደርጉታል፡፡ ገዳማቸውን እንደገፍ በዓታቸውን እናጸና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: