«ጊቤ» መርከብ ከሆርሙዝ ሰርጥ ስጋት ወጥታ ወደ ሀገር እየተመለሰች ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በቅርቡ በአሜሪካ፣ እስራኤል እና ኢራን መካከል በተፈጠረው ከፍተኛ ውጥረት ሳቢያ ለወራት በሆርሙዝ ሰርጥ ተይዛ የነበረችው የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ መርከብ ” ጊቤ” ከነ ጭነቷ በሰላም ወደ አጎራባች ጅቡቲ ወደብ እየተጓዘች መሆኑ ተሰማ።

በመላው ዓለም በ347 የወደብ መዳረሻዎች ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ከሚያውለበልቡ መርከቦች መካከል አንዷ የሆነችው ይህቺ መርከብ በአሁኑ ወቅት በኦማን ባህረ ሰላጤ አካባቢ የምትገኝ ሲሆን እ.አ.አ ሰኔ 28 ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ መዳረሻዋ ጅቡቲ ወደብ እንደምትደርስ ይጠበቃል።

​ይህ ዜና የተሰማው በሆርሙዝ ሰርጥ አካባቢ የነበረውን ከፍተኛ ዕለታዊ የደኅንነት ስጋትና ውጥረት በጽናት ተቋቁመው ሀገራዊና ሙያዊ ክብራቸውን ባስጠበቁት ጀግና መርከበኞች ጥረት ሲሆን መርከቧ ወደ ቀደመው የጉዞ መስመሯ መመለሷ ለመላው ኢትዮጵያውያን ትልቅ እፎይታ ሆኗል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: