በጋምቤላ ክልል አጭር ቀሚስ የሚለብሱ ሴቶች 3ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ እየተቀጡ ነው ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

በጋምቤላ ክልል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመቆጣጠርና የህፃናትን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ውሳኔዎች በመተግበር ላይ እንደሚገኙ የክልሉ አኙዋ ብሔረሰብ ዞን የአቦቦ ወረዳ ሴቶቸና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል። ውሳኔዎቹ ሊተላለፉ የቻሉት ልጆች ከወላጆች አቅም በላይ በመሆናቸው እና ትዕዛዝ ባለመስማታቸው ነው ሲል ፅ/ቤቱ አስታውቋል ።

ወላጆች መንግስት ይደግፈን ባሉት መሠረት ፕሮፖዛል ተቀርጾ እና ኮሚቴ ተዋቅሮ ፣ከፖሊስ ፣ከፍትህ እና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ጥቃቶችን ለመከላከል በሚያስችሉ ውሳኔዎች ላይ እየተሰራ ይገኛል ። የአቦቦ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ አዊሊ ኡጁሉ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ሴቶች የሚለብሷቸው አጭር ቁመት ያላቸው ልብሶች የጥቃት ተጋላጭነትን ይጨምራሉ።

ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲከታተሉና ልጆችም ከዚህ አይነቱ ድርጊት እንዲቆጠቡ የሚያስችሉ ጥብቅ መመሪያዎች መተላለፋቸውን ተናግሯል ።ይህንን ችግር ለመቅረፍ ለጥቃት አጋላጭ በሆነ መልኩ አጭር ልብሶችን ለብሰው በሚንቀሳቀሱ ሴቶች ላይ የ3ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት መተላለፉን የተናገሩት ኃላፊዋ መመሪያውን ተላልፈው በተገኙት ላይ የቅጣት እርምጃ እየተወሰደ ይገኛል ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል ።

ዘገባው የብስራት ሬዲዮ ነው


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1