ልብ ሰባሪው የሞት ዜና

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​ከሁለት ወር በኋላ በጋብቻ ለመቀላቀል እና አዲስ ህይወትን ለመጀመር ተስፋ ሰንቀው የነበሩ ጥንዶች፣ ባልታሰበ የሞት ዜና መለያየታቸው ታወቀ። እጮኛዋን በሞት የተነጠቀችው ወጣት፣ በሃዘን የተሞላ የመሰናበቻ መልዕክቷን በማህበራዊ ሚዲያ ይፋ አድርጋለች።

​ወጣቷ ሙሽራ በፃፈችው የሃዘን መግለጫ፣ የሟች እጮኛዋን መልካም ስነ-ምግባር እና ለእሷ የነበረውን ፍቅር በቁጭት ገልጻለች። “ያንተን ያህል የሚወድ፣ የሚያከብርና በጸሎቱ የሚጠብቀኝ ቅን ሰው አጣሁ” ስትል ስሜቷን ተናግራለች። በአጭር ጊዜ ውስጥ ለእሷ እውነተኛ ደስታን የሰጠ መሆኑን የጠቀሰችው ወጣቷ፣ በጋራ ለመመስረት ያሰቡት ህይወት በሞት መቋረጡን በሃዘን አስታውሳለች።

​የሟች እጮኛዋን በሰላም እንዲያርፍ መልካም ምኞቷን የገለጸችው ወጣቷ፣ በልቧ እና በፀሎቷ ሁሌም እንደምትዘክረው በመግለጽ የመጨረሻ የፍቅር አደራዋን አስተላልፋለች።

​ለሟች ቤተሰቦች፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለሙሽራይቱ መጽናናትን እንመኛለን።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: