ከሚሰራበት ድርጅት ውስጥ ተሽከርካሪ በመሰወርና አካሉ እንዲበተን ያደረገ ግለሰብ ከስድስት ግብረ አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ

- Advertisement -
Sidebar AD

ከሚሰራበት ድርጅት ውስጥ ተሽከርካሪ በመሰወርና አካሉ እንዲበተን ያደረገ ግለሰብ ከስድስት ግብረ አበሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር ዋለ።

አበራ መረሳ የተባለው ተጠርጣሪ ወንጀሉን የፈፀመው ሰኔ 5 ቀን 2018 ዓ/ም በአሽከርካሪነት ተቀጥሮ ከሚሰራበት ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ስታዲየም አካባቢ ከሚገኝ አንድ የኮንስትራክሽን ድርጅት ነው፡፡

ተጠርጣሪው ወንዶሠን አባተ፣ ሶይብ ሙኒር፣ ክንዱ ደጉ፣ ስንታየሁ ተመስገንን፣ ብሩክ ግርማ፣ ባህሉ ሲሳይ ከተባሉ አባሪዎቹ ጋር በመመሳጠር ግምቱ 18 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 48 4 05 HILUX ፒካፕ ተሽከርካሪን ከድርጅቱ ይዞ በመውጣት ከአንድ ግለሰብ ጋር በ 6መቶ ሺ ብር ለመሸጥ ተስማምቷል።

ግለሰቡ ቀደም ብሎ የሽያጩን ቀብድ 110 ሺህ ብር በመቀበልና ከግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን አዳማ ከተማ ላይ የተሽከርካሪውን አካል በመነቃቃልና በመበታተን በአንድ መጋዘን ውስጥ አስቀምጧል፡፡

የወንጀል ድርጊቱን ሲያጣራ የነበረው በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ሲሆን ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ/ም ከሀገር መከላከያ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት እንዲሁም ከአዳማ ከተማ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑ በአጠቃላይ 7 ተጠርጣሪዎችን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ሊያውልም ችሏል፡፡

የመንግስትም ሆና የግል ድርጅቶች ሠራተኞችን ሲቀጥሩ የሠራተኞቻቸውን ማንነት የሚገልጽ አስፈላጊ ሠነዶች አሟልተው መሆን እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።






Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: