በምግብ አመጋገባችን ላይ የምንሠራው ታላቁ ስህተት

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ሰዎች ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ በጤናቸውና በአካላዊ ብቃታቸው ላይ ለሚከሰቱት መዳከሞች ዋነኛው መንስኤ በዕለታዊ የምግብ አመጋገባቸው ላይ የሚሠሩት ስህተት መሆኑ ይነገራል። በአሁኑ ወቅት የበርካታ ሰዎች የምግብ ገበታ በአብዛኛው በስታርች (እንደ እንጀራ፣ ሩዝ፣ ዳቦና ፓስታ ባሉ) እንዲሁም በቅባት የተሞላ ሲሆን ለሰውነት ግንባታ እጅግ አስፈላጊ የሆነው ፕሮቲን ግን ትኩረት ተነፍጎት ይታያል።

ይህ ዓይነቱ የተሳሳተ የአመጋገብ ልማድ ዓመታት ሲነጎዱ ለጡንቻዎች መኮማተር ለአጠቃላይ አቅም መዳከምና ደረጃዎችን የመውጣት ያህል ቀላል የሚባሉ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች እንኳ ፈታኝ እንዲሆኑ እያደረገ ይገኛል።

​የሰው ልጅ አካል፣ ጡንቻዎች፣ የውስጥ አካላት፣ ሆርሞኖች እና በሽታ የመከላከል ሥርዓት የተገነቡት ከፕሮቲን እንጂ ከስታርች ባለመሆኑ በዕድሜ የመግፋት ሂደት ውስጥ ጤናማና ንቁ ሆኖ ለመቀጠል ከፍተኛ ጥራት ያለውን ፕሮቲን ማግኘት ወሳኝ ነው።

በዘርፉ ኤክስፕርት የሆኑት ዶ/ር ቤሪ ምክረ ሃሳብ ያላቸው ሲሆን እንደ ሥጋ፣ ዓሣ፣ እንቁላል እና አይብ ያሉ ምግቦች ሰውነት ራሱን በየቀኑ ለመጠገንና ጡንቻን ጠብቆ ለማቆየት የሚያስፈልጉትን አሚኖ አሲዶች በከፍተኛ ጥራትና መጠን ይዘዋል። ምንም እንኳ እንደ ባቄላ ያሉ ጥራጥሬዎች የፕሮቲን ምንጭ ቢሆኑም ከከፍተኛ ስታርች ጋር የተቀላቀሉ በመሆናቸው እንደ እንስሳት ተዋጽኦዎች ሙሉና ጥራት ያለው አሚኖ አሲድ ሊሰጡ እንደማይችሉ ተገልጿል።

​ለጤናማ እርጅና እና ራሱን የቻለ ገለልተኛ ሕይወት ለመምራት ዋነኛው መለኪያ የካሎሪ ቁጥርን መቀነስ ሳይሆን በሰውነት ውስጥ ያለውን የጡንቻ መጠን ጠብቆ ማቆየት ነው። ከ20 እና ከ30 ዓመታት በኋላ የምንኖርበትን ጤናማ አካል የምንገነባው ዛሬ በምንመገበው ምግብ በመሆኑ በምግብ ገበታችን ላይ ለውጥ በማድረግ ፕሮቲንን(በጣም ሳይበዛ) ዋነኛው የገበታችን መሠረት እንጀራና መሰል ስታርቾችን ደግሞ ማሟያ ብቻ ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶታል።

በርግጥ ሐኪሙ በየቀኑ ይህ መሳይ የአመጋገብ ስርአት ለመፍጠር የገንዘብ ምንጩ ከየት እንደሆነ የገለጹት ነገር ስለሌለ አቅም በፈቀደ በተገኘው አጋጣሚ ይህን እንድታደርጉ እንላለን።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: