#Ethiopia | በኢትዮጵያ የሚገኙት ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ እና ወርልድ ቱጌዘር (World Together) በጋራ በመሆን ‘ዘ ፋይናል ሳሉት’ (The Final Salute) የተሰኘ የድጋፍ ፕሮጀክት ይፋ አድርገዋል።
ድጋፉ የኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞች ማህበር በመተባበር የሚደረግ ሲሆን በኮርያ ጦርነተ ለተሳተፉ አርበኞች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው።
ይህ የ12 ወራት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞችን ታሪክ ለማክበር እና ያላቸውን ምኞት ለማሳካት ያለመ መሆኑን ነው የተገለጸው።
በአሁኑ ወቅት በህይወት የሚገኙት 46ቱ አርበኞች በአብዛኛው ከ90 ዓመት በላይ የሆናቸው ሲሆን፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ቢገጥሟቸውም ከኮሪያ ጋር ያላቸውን ታሪካዊ ትስስር ከፍ አድርገው እንደሚመለከቱ ተገልጿል።
ለዚህም አስፈላጊው የልብስ ወጪ ይሸፈናል፤ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸው በኮሪያኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎች በተቀረጸ የመታሰቢያ መልእክት የታጀቡ ትላልቅ የፎቶ ምስሎች ይሰጣቸዋል ተብሏል።
በቃለ መጠይቅ አማካኝነት አምስት አርበኞች ተመርጠው እንደ የቤተሰብ መገናኘት፣ የህክምና ድጋፍ ወይም ወደ ደቡብ ኮሪያ የመመለስ ጉዞ ያሉ የረጅም ጊዜ ምኞቶቻቸው ይፈጸማሉ።
ፕሮጀክቱ የአርበኞቹን ፎቶግራፎች እና ዘጋቢ ፊልሞች የሚያሳይ የህዝብ ኤግዚቢሽን እና ለእነሱ ክብር የሚሰጥ ዝግጅት ያደርጋል ተብሏል።
ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ከ2012 ጀምሮ ለኢትዮጵያ የኮሪያ ጦርነት አርበኞች እና ቤተሰቦቻቸው በትምህርት፣ በኑሮ ማሻሻያ እና በቤቶች ድጋፍ እያደረገ የሚገኝ ተቋም ነው።
ለዚህ መርሀ ግብር የገንዘብ ድጋፉን የሚያደርገው ኤልጂ ኤሌክትሮኒክስ ነው ተብሏል።
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ኤልጂኤሌክትሮኒክስ
#ወርልድቱጌዘር
#ኮርያኤምባሲ
#የኮርያዘማቾችማህበር
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgen
#mediacommunication



Source: GetuTemesgen









No comments yet.