የአዲስ ኪዳን ካህናት ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን የ10ኛ ዓመት በዓሏንና የ‘መልካም ወጣት ደማስቆ’ ፕሮጀክትን ልታስጀምር ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

የአዲስ ኪዳን ካህናት ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን የ10ኛ ዓመት በዓሏንና የ‘መልካም ወጣት ደማስቆ’ ፕሮጀክትን ልታስጀምር ነው

#FastMereja I የአዲስ ኪዳን ካህናት ኢንተርናሽናል ቤተክርስቲያን የ10ኛ ዓመት የምስረታ በዓሏን እና የ“መልካም ወጣት ደማስቆ 2018” መርሃ-ግብር መክፈቻን አስመልክቶ ዛሬ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥታለች።

ቤተክርስቲያኗ በዓሉንና የመክፈቻ ፕሮግራሙን አስመልክቶ ከሰኔ 21 እስከ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በቅጥር ግቢዋ ልዩ መንፈሳዊ መርሃ-ግብር ማዘጋጀቷን በመግለጽ፣ መላው ህዝብ በበዓሉ ላይ እንዲገኝ ጥሪ አቅርባለች።

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተብራራው፣ ተቋሙ ባለፉት አስር ዓመታት ወንጌልን ከመስበክ ባለፈ በማርሲል ንጹህ ውሃ ፕሮጀክት አማካኝነት በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ማህበረሰቦችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ ሲሆን፣ በማህበራዊ ኃላፊነት ዘርፍም በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል።

የቤተክርስቲያኗ ትልቁ ሀገር አቀፍ ፕሮጀክት የሆነው “መልካም ወጣት” ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ከ200 ሺህ በላይ ወጣቶችን ማሳተፍ መቻሉ የተገለጸ ሲሆን፣ ዘንድሮ የሚካሄደው “መልካም ወጣት ደማስቆ 2018” የተሰኘው መርሃ-ግብር 5 እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ እንደሚከናወን ታውቋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2