የዓለም አቀፉ አግሮ-ማኑፋክቸሪንግ እና የቡና ንግድ ትርዒት ተጀመረ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I 8ኛው አግሮ ፉድ ፕላስትፕሪንትፓክ ኢትዮጵያ እና 2ኛው የኢትዮጵያ ቡናና ምግብ ንግድ ትርዒት በዛሬዉ እለት በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር በይፋ ተከፈተ።

ዝግጅቱን የሀገር ውስጥ ቀዳሚ የንግድ ትርዒት አዘጋጅ የሆነው ፕራና ኢቨንትስ ከጀርመን አጋሩ ፌርትሬድ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሲሆን፣ ዓላማውም መንግስት ኢትዮጵያን በአፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ ለጀመረው እንቅስቃሴና ለግብርና ማቀነባበሪያ (አግሮ-ፕሮሰሲንግ) ዘርፍ ድጋፍ መስጠት መሆኑ ተገልጿል።

ከሰኔ 18 እስከ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ላይ ከ19 ሀገራት የተውጣጡ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍና ሀገር በቀል ኩባንያዎች እንደሚሳተፉ ተነግሯል።

ከተሳታፊዎቹ መካከልም ብራዚል፣ ቻይና እና ጣሊያን በብሄራዊ ደረጃ (Pavilion) ሰፊ ምርትና ቴክኖሎጂ ይዘው የሚቀርቡ ሲሆን፤ ጀርመን፣ ፈረንሳይ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ኬንያ፣ ግብፅና ጅቡቲን ጨምሮ ሌሎችም ሀገራት ምርትና አገልግሎታቸውን እንደሚያስተዋውቁ ተገልጿል።

ኤግዚቢሽኑ በዋናነት በግብርና፣ በምግብና መጠጥ ግብዓቶች፣ በላቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንዲሁም በፕላስቲክ፣ በህትመትና በማሸጊያ (Packaging) ዘርፎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪም በምግብና በቡና እሴት ሰንሰለት ላይ ትኩረት ያደረገ ጥምር የንግድ ትርዒት እንደሚሆን ተመልክቷል።

በመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የግብርና፣ የኢንዱስትሪ እንዲሁም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች፣ የልዩ ልዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የንግድ ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: