#Ethiopia | የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፖለቲካ ጣልቃገብነት ተላቀው ነጻ የእውቀትና የሃሳብ ማፍለቂያ እንዲሆኑ የሚያስችል የሪፎርም ስራ እየተከናወነ መሆኑን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለጹ።
ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው መድረክ ላይ እንደተብራራው፣ የዚህ ታሪካዊ ሽግግር ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ-ገዝነት በማሸጋገር ለእውነትና ለእውቀት ቁርጠኛ የሆኑ፣ ሀገራቸውን የሚወዱና የሚለውጡ ዜጎችን ማፍራት ነው።
ለዚህም ስኬት ተቋማቱ በዘላቂ የውስጥ ገቢ ማስገኛ መንገዶች ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩና የአቅም ግንባታ ስራዎችን እንዲያጠናክሩ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ይህን የራስ-ገዝነት ዝግጁነት በውል ለመገምገም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 9 ገለልተኛ የባለሙያ ቡድኖችን በ9 ተለይተው በታወቁ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ አሰማርቶ ጥናታዊ ምልከታ አድርጓል።
በዚህ ታሪካዊ የዝግጁነት ግምገማ ውስጥ የተካተቱት የጅማ፣ የሀዋሳ፣ የአርባ ምንጭ፣ የሐረማያ፣ የጎንደር፣ የባህርዳር፣ የመቀሌ፣ የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ሲሆኑ፣ በቀጣይም ግኝቶቹን መሰረት በማድረግ በማስረጃና በሀገራዊ ሃላፊነት ላይ የተደገፉ የሽግግር ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ከት/ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
#Ethiopia #EducationReform #HigherEducation #UniversityAutonomy #MoE #EthiopianUniversities


Source: GetuTemesgen









No comments yet.