ጦርነቱን ለማስቆም የተደረገው ስምምነት ‘የአሜሪካ ሽንፈት’ መግለጫ ነው ስትል ኢራን ተናገረች
ጦርነቱን ለማቆም በኢራን እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል የተደረገው ስምምነት “የአሜሪካ ሽንፈት መግለጫ” ነው ሲሉ የኢራን ተደራዳሪ ቡድን መሪ መሀመድ ባገር ጋሊባፍ ተናግረዋል።ጋሊባፍ በአዘርባጃን በኢራን ቴሌቪዥን ስርጭት ላይ በተላለፈዉ መልዕክታቸዉ እንደተናገሩት “የኢስላማባድ ስምምነት የግፊት እና የማስገደድ ውጤት ሳይሆን የጀግናው የኢራን ህዝብ ተቃውሞ እና ስልጣን ውጤት ነው” ብለዋል።
በዚህም የኢስላማባድ የመግባቢያ ስምምነት የአሜሪካን ሽንፈት ማወጅ ሆኗል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ከፍተኛ ተደራዳሪው መሀመድ ባገር ጋሊባፍ የመካከለኛው ምስራቅ የጸጥታ መዋቅርን የክልሉ ሀገራት ብቻ መወሰን አለባቸው ብለዋል።”የውጭ ወታደራዊ ሃይሎችን ከአካባቢው መውጣት እንደ ስልታዊ አላማ እንቆጥረዋለን።የቀጣናው የወደፊት እጣ ፈንታ በግጭት ሳይሆን በመስተጋብር እንዲወሰን በመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት የሚገኙ ከክልል ውጭ ያሉ ወታደራዊ ኃይሎች የአለመረጋጋት መንስኤ ናቸው ሲሉ አክለዋል።
ጋሊባፍ ወደ ባኩ አዘርባጃን ባደረጉት ጉዞ እንደተናገሩት ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ ከሚገኙ ሀገራት ጋር “በውስጣዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ ባለመግባት እና ሉዓላዊነትን በማክበር” ላይ ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል ።እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ ላይ የምታደርገውን ጥቃት እና ወረራ ማቆም አለባት በማለት የኢራንን አቋም ደግመዋል።
በስምዖን ደረጄ
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.