በአማራ ክልል ፍቺ የሚፈፅሙ ጥንዶች ቁጥር ጭማሪ አሳይቷል ተባለ
በአማራ ክልል ባለፉት 11 ወራት በሁሉም ኩነቶች ከ667 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ምዝገባ ማከናወኑን የክልሉ ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አስታውቋል ።በአገልግሎቱ የእቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት አቶ ዋለ ቅዱስ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት ባለፉት 11 ወራት 7 ሺህ 965 ፍቺዎችን ለመመዝገብ ዕቅድ ተይዞ ነበር ።
ይህንን መነሻ በማድረግ በወቅታዊ ፣በዘገየ እና የጊዜ ገደቡ ባለፈ ምዝገባ 3 ሺህ 977 ፍቺዎችን መመዝገብ እንደቻለ የገለፁት አቶ ዋለ በዚህም የዕቅዱን 50 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል ።ባለፈው አመት በተመሳሳይ ወቅት ላይ የተመዘገበው የፍቺ መጠን 1 ሺህ 616 እንደነበር ተገልጿል ።
በዚህ ጊዜ ውስጥ ከአምናው በተሻለ መልኩ ምዝገባ ማካሄድ የተቻለ ቢሆንም ከዚህ የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር ከፍርድ ቤቶችና ከአጋር አካላት ጋር አገልግሎቱ ተቀራርቦ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግሯል።የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን አለማስመዝገብ ስለሚያስከትለው ጉዳት ህብረተሰቡ በቂ እውቀት እንዲኖረው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አገልግሎቱ ገልጿል።
ሀሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት በ570 የምዝገባ ጣቢያዎች ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምዝገባ እየተካሄደ ይገኛል ተብሏል።
በመባ ወርቅነህ
@Seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.