“የማስተርስ ትምህርት ወደ 4 ዓመት ሊያድግ ይገባል ” ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

የአሰራር ለውጥ ካልተደረገ ወደፊት ለሚመረቁ ተማሪዎች እውቅና ለመስጠት ትልቅ ተግዳሮት ይፈጥራል ብሏል የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን

በኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሰጠው የሁለተኛ ዲግሪ (የማስተርስ) ትምህርት ፕሮግራም ከሁለት ዓመት ወደ አራት ዓመት ሊያድግ እንደሚገባ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ይህንን ያስታወቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቋሚ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት የ11 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰጠው ሙያዊ ማብራሪያ፣ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ በሁለት ዓመት መደበኛ መርሃ ግብር እየተሰጠ ያለው የማስተርስ ትምህርት፣ አዲስ ከጸደቀው የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብና ከአለም አቀፍ በተለይም ከአውሮፓ ስታንዳርድ ጋር የማይገናኝ ሆኖ ተገኝቷል።

ይህ ክፍተት በአስቸኳይ የማይስተካከል ከሆነ፣ ወደፊት ለሚመረቁ ተማሪዎች የትምህርት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ወይም እውቅና (Authentication) ለመስጠት ትልቅ ተግዳሮት እንደሚሆን ባለስልጣኑ አስገንዝቧል።

ከእነዚህም መካከል በሀገራችን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ሳያመጡ ወደ ውጭ ሀገር ሄደው ከተማሩ በኋላ፣ ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ የሚጠይቁት የብቃት ማረጋገጫ ጉዳይ ትልቅ አነጋጋሪ አጀንዳ ሆኗል።

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ2017 ዓ.ም ያጸደቀው የኢትዮጵያ የትምህርትና ስልጠና የብቃት ማረጋገጫ ማዕቀፍ ደንብ፣ እውቅና ካላቸው የውጭ ሀገር የትምህርት ተቋማት የተገኙ የብቃት ማረጋገጫዎች በሀገሪቱ መመዘኛ መሰረት ተመዝነው እውቅና እንዲሰጣቸው ቢደነግግም፣ አሁን ያለው አሰራር ግን ይህንን ለመተግበር አስቸጋሪ አድርጎታል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዳመለከተው፣ ለአማራጭ የትምህርት ክሬዲት ስርአት (ECTS) በአውሮፓ (ከፍተኛ) የሆነው መስፈርት፣ በኢትዮጵያ ደንብ ውስጥ ‘ (ዝቅተኛ) ሆኖ ተቀምጧል። ይህንን ወደ ዓመት ሲተረጎም የማስተርስ ፕሮግራም ደንቡ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ የ4 ዓመት ፕሮግራም መሆን እንዳለበት ያስገድዳል።

ጉዳዩን በተመለከተ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም ለትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ ቢገለጽም እስካሁን ምንም ምላሽ አልተገኘም ተብሏል፡፡

ዘገባው የኢትዮ ኤፍ ኤም ነው!


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1