አገር አቀፍ ፈተና እና የሴቶች #የወርአበባ ንፅህና መጠበቂያ

- Advertisement -
Sidebar AD

በወር አበባ ምክንያት #ሴት ተማሪ መሸማቀቅ የለባትም!

#Ethiopia | እንደሚታወቀው የሰኔ ወር የ 6ኛ; የ 8 ኛ እና የ 12 ኛ ክፍሎች የአገር አቀፍ እና ክልላዊ ፈተናዎች የሚሰጥበት ወቅት ነው።

ከሰኔ ወርም ቀደም ተብሎ የመንግስትና የግል ት/ቤቶች እና የትምህርት ሚኒስቴር; ቢሮዎችና ፅ/ቤቶች ተማሪዎች በጥሩ ውጤት ፈተናዎቹን እንዲያልፉ በትጋት ተማሪዎቻቸውን ያዘጋጃሉ።

የፈተና ቁሳቁሶች; ጥያቄዎች; የመፈተኛ ት/ቤቶች; ፈታኝ መምህራን እና ሌሎችንም ቀድመው ለማዘጋጀት የሚደረገው ርብርብ የሚደነቅ ነው። ለወላጆችም/ለቤተሰቦችም ልጆቻችንን ለፈተናዎቹ በአግባቡ እንድናዘጋጅ ተደጋጋሚ መልእክቶችና ማስጠንቀቂያዎች ይላኩልናል።

በተለይ ፈተናዎቹ ቀናቸው እየቀረበ ሲመጣ ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ ይዘው መምጣት ያለባቸው እና ይዘው ለመምጣት የሚከለከሉ ቁሳቁሶች ለተማሪዎቹም ተደጋግሞ ይነገራቸዋል ለእኛም ለወላጆች/ቤተሰቦች ማስጠንቀቂያ ይላክልናል።

ተማሪዎቹ በፈተና ቦታው ይዘው መምጣት የሚፈቀድላቸው :-
1)እርሳስ ; ላጲስ; መቅረጫ
2)የት/ቤት መታወቂያ እና admission card #ብቻ ነው።

አንድ ትልቅ ነገር ግን ተረስቷል #ሞዴስ !

እንደ አገር ትልቅ ዝግጅት የምናደርግለት አገር አቀፍ ፈተና ላይ ሴት ተማሪዎች በፈተና ወቅት #የወር አበባ ላይ ከሆኑ የንፅህና መጠበቂያ #ሞዴስ እንደሚያስፈልጋቸው መዘንጋት ማለት የፈተናው ዝግጅት; ሂደት እና አፈፃፀም #በስርአተ-ፆታ እይታ እንዳልተቃኘ ማሳያ ነው።

እንኳን ፈተና ተጨምሮበት ይቅርና ወር አበባ ሴት ታዳጊዎች ላይ ከባድ የአካል #ህመም; #የሆርሞን መዛባት እና #የስነልቦና ጫና ያሳድርባቸዋል።

ስለዚህ የወር አበባ + ፈተና የትምህርት ዘርፉ እና ት/ቤቶች ለሴት ተማሪዎች የተለየ ትኩረት እንዲሰጡ ግድ የሚላቸው ጉዳይ ነው።

ፈተና እየተፈተኑ ድንገት የወር አበባቸው የሚመጣባቸው እና የወር አበባ የሚበዛባቸው /heavy flow period / ሴት ተማሪዎች ቶሎ #ምዴስ መቀየር ወይም መጠቀም ሰላለባቸው በፈተና ወቅት ሞዴስ ይዘው እንዲገቡ ባልተፈቀደበት ሁኔታ ሴት ተማሪዎቹ ከአሁን አሁን ልብሴ ተበላሸ ብለው #ሲሳቀቁ ለፈተናው የሚሰጡት #ትኩረት ይጎዳል ።በዚህም የተነሳ ውጤታቸው ላይ #አሉታዊ ተፅእኖ ያመጣል።

ታዲያ የፈተናው ጣቢያዎች ለሴት ተማሪዎች በመፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የድንገተኛ ግዜ #ሞዴስ /emergency sanitary pad / ሊያስቀምጡ ይገባል። አለበለዚያ ፈተናው ለሴት ተማሪዎች #ኢፍትሀዊ ይሆናል።

አንዲትም #ሴት ተማሪ #በተፈጥሮ ምክንያት #ከወንድ ተማሪዎች ወደኋላ መቅረት የለባትም!
የህግ ባለሙያ ሜሮን አራጋው


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: