ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ የሚመሯት ሀገር ተመሠገነች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የቡርኪና ፋሶ ፕሬዚዳንትና የሀገሪቱ መሪ ካፒቴን ኢብራሂም ትራኦሬ ሰኞ ጠዋት የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ማዕከላዊ ባንክ (BCEAO) ገዥ ከሆኑት ከዣን ክሎድ ካሲ ብሩ ጋር በፅሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

በኦጋዱጉ ቆይታቸው የባንኩ ገዥ ሚስተር ዣን ክሎድ በንዑስ ቀጠናው ያለውን አጠቃላይ የኢኮኖሚ የገንዘብና የፋይናንስ ሁኔታ ጤናማነት በስፋት ለመገምገም ጥሩ ዕድል የፈጠረላቸው ሲሆን በዚህ መሃል የቡርኪና ፋሶን አስደናቂና አበረታች የኢኮኖሚ አፈጻጸም በተለየ ሁኔታ አድንቀዋል።

ውይይቱ ሀገሪቱ እያሳየች ያለችውን ጠንካራ የኢኮኖሚ ጉዞ ከማሳየቱም በላይ በቀጠናው ያላትን የፋይናንስ መረጋጋት ሚና በግልጽ ያረጋገጠ ሆኖ አልፏል።

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: