በትራማዶል እጅጌውን ሞልቶ ለማቆያ ቤት ተጠርጣሪዎች ሊያቀብል የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

- Advertisement -
Sidebar AD

በህግ ቁጥጥር ስር ለዋሉ ተጠርጣሪዎች “ትራማዶል” የተባለ አበረታችና እጽ መሰል መድኃኒት በምስጢር ለማስገባት የሞከረ ግለሰብ እጅ ከፍንጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።

ብርሃኑ ወንድሙ የተባለው ይህ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር የዋለው ሰኔ 17 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ መሆኑ ተገልጿል።

ግለሰቡ በወንጀል ተጠርጥረው በማቆያ ቤት የሚገኙ ግለሰቦች የፍርድ ቤት ቀጠሯቸው ከመድረሱ አስቀድሞ መድኃኒቱን ለማድረስ አቅዶ ነበር። ለዚህም ይረዳው ዘንድ የለበሰውን ጃኬት እጅጌ በመቅደድ 39 ፍሬ ትራማዶል የተባለ አበረታች መድኃኒት በውስጡ በመደበቅ ወደ ማቆያ ቤቱ ለመግባት ሞክሯል።

ሆኖም በማቆያ ቤቱ መግቢያ ላይ በተደረገበት ጥብቅ ፍተሻ ወንጀሉ መክኖ እራሱ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል። ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ተገቢውን ምርመራ እያጠናከረ መሆኑንና በአቃቤ ህግ አማካኝነት ክስ እንደሚያመሰርትበት አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን አስቀድሞ ለመከላከል በማቆያ ቤቶች አካባቢ የሚደረገው ጠንካራ ቁጥጥርና ፍተሻ ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መልዕክቱን አስተላልፏል።



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: