‹‹በ4 አቅጣጫ የከበበንን ጠላት ብቻውን አስቀርተንዋል›› ጀነራል ጆን መዲድየሕወሓት ጀነራሎች እና ወታደራዊ መኮንኖች የሚያሰሙ…

- Advertisement -
Sidebar AD
‹‹በ4 አቅጣጫ የከበበንን ጠላት ብቻውን አስቀርተንዋል›› ጀነራል ጆን መዲድ
የሕወሓት ጀነራሎች እና ወታደራዊ መኮንኖች የሚያሰሙት ዛቻ እና ፉክራ ቀጥሏል፡፡ የትግራይ ሕዝብ ለጦርነት ድቤ ድለቃቸው ጆሮውን ቢነፍጋቸውም በግድ በጦር ሜዳ ሊማግዱት በየአደባባዩ የ‹እናሸንፋለን› ፉከራ እያሰሙ ነው፡፡
ከትግራይ ጦር አዛዦች መሀል አንዱ የሆኑት ጀነራል ዩሀንስ ወልደጊዮርጊስ (ጆን መዲድ) በዎይን ሚዲያ በኩል የተለመደ ክስ እና የእናሸንፋለን ፉከራ አሰምቷል፡፡ ጀነራሉ፣ ‹‹በአራት አቅጣጫ የከበበንን ጠላት አሰላለፍ በጣጥሰን፣ ብልጽግናን ብቻውን አስቀርተንዋል›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ ትናንት ተባብረው የዘመቱብንን ኃይሎችን በታትንን፣ በቀጠናው አዲስ አሰላለፍ ፈጥረናል የሚሉት የጦር አዛዡ፤ አልተቋጨም ያሉትን ህልውና ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን ነው ብለዋል፡፡“ጠላቶቻችን ብዙ ነገር እያሰቡ ነው፤ ብዙ ነገር ደግሞ ይፈርስባቸዋል” ሲሉም አክለዋል፡፡
ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ አዲስ የኃይል አሰላለፍ እንዲፈጠር አድርገናል የሚሉት ጀነራሉ፤ ‹‹በ2013 ከጎረቤት ሀገራት እሰከ ሀገር ውስጥ ኃይሎች አስተባብሮ የዘመተብንን ጠላት ብቻውን አስቀርተን፣ የራሳችን አሰላለፍ ፈጥረናል›› ብለዋል፡፡  “በዚያን ጊዜ ተፈጥሮ የነበረውን እኛን የማጥፋት አሰላለፍ በትነን፣ ከሀገር ውስጥ እና በምስራቅ አፍሪካ አዳዲስ የአሰላለፍ ለውጦች መፍጠር ችለናል›› ነው ያሉት። ጆን መዲድ አዲስ አሰላለፍ ፈጥረናል የሚሉት ጽምዶን ነው፡፡
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: