#Fastmereja: በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የለቡ ምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ሕንፃ ቤተክርስቲያን፣ ቀሪውን 10 በመቶ የግንባታ ሥራ አጠናቆ በ2019 ዓ.ም ለመመረቅ ታላቅ ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ማዘጋጀቱን የደብሩ አስተዳደር አስታወቀ።
የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ጽዮን ቆሞስ አባ እስጢፋኖስ፣ ሰበካ ጉባኤው እና የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት የሕንፃ ቤተክርስቲያኑ አጠቃላይ ግንባታ 90 በመቶ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዉ ቀሪውን ሥራ ሙሉ በሙሉ አጠናቆ ለታላቁ ምረቃ ለማብቃትም 135 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።
የቤተክርስቲያኑ ግንባታ ከተጀመረ 13 ዓመታት ገደማ የፈጀ ሲሆን፣ ለዚህም በዋናነት ግንባታው ሙሉ በሙሉ በምእመናን መዋጮ የሚካሄድ መሆኑ፣ የገባውን ቃልኪዳን ሙሉ በሙሉ አለመፈጸም፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰትና ተያያዥነት ያላቸው የምእመናን ከቤተክርስቲያን መራቅ በምክንያትነት ተጠቅሰዋል።
የቤተክርስቲያኑ አስተዳደር የግንባታው መጓተትና መዛል ማክተም እንዳለበት በመግለጽ፣ በመላው ዓለም የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንና የቅዱሳኑ ወዳጆች ለቤተክርስቲያኑ ፍጻሜ ታሪካዊ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ጥሪ አቅርቧል።
ለዚህም ታላቅ ዓላማ ስኬት ሰኔ 27 እና 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ሥርጭት የሚተላለፍ ዓለም አቀፍ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ተዘጋጅቷል።
ምእመናን በገንዘብ ከመደገፍ ባለፈ እንደ ስዕለ አድህኖ፣ በር እና መስኮት ማሠራት፣ የቤተሰብ ስም ማጻፍ እንዲሁም የመብራትና ምንጣፍ አቅርቦቶችን ማሟላትን በመሰሉ የአይነት ድጋፎች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑም ተገልጿል።
የደብሩ አስተዳደር ምእመናን በቀጥታ ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ የሚከተሉትን የባንክ አካውንቶችና የፈጣን መረጃ ስልክ መስመሮች ይፋ አድርጓል፦
የባንክ አካውንት ቁጥሮች፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000033449228
አባይ ባንክ፦ 1112119589181030
ሕብረት ባንክ (አጭር ቁጥር)፦ 1906
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (አጭር ቁጥር)፦ A1906
ለተጨማሪ መረጃ:- 0911231045 / 0943111865/0910662112 / 0911200730 / 0912851096 የስልክ መስመሮች መገናኘት እንደሚቻል ተገልጿል።



Source: FastMereja








No comments yet.