የቤት ኪራይ በተመን ሊወሰን ነው‼️
ከ2019 ጀምሮ የቤት ኪራይ ዋጋ በአዲስ መተመኛ ሊወሰን ነው።
በአዲስ አበባ ከተማ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋን ፍትሃዊ፣ ሳይንሳዊና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ለመወሰን የተዘጋጀ የዋጋ መተመኛ ጥናት ዛሬ ቀርቦ በባለድርሻ አካላት ፊት ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ቅድስት ወልደ ጊዮርጊስ እንደገለጹት፣ ከተማ አስተዳደሩ የኑሮ ጫናን ለመቀነስ እና በቤት ኪራይ ገበያ ውስጥ የተስፋፉ ሕገ-ወጥና ዘፈቀዳዊ አሰራሮችን ለመግታት በተከታታይ እየሰራ ነው።
እንደ ኃላፊዋ ገለጻ፣ በ2016 ዓ.ም. የተከናወነው ሰፊ የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባ በዘርፉ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ አሁን የቀረበው የኪራይ ዋጋ መተመኛ ጥናትም የውል ማደስ ሂደትን ፍትሃዊና ግልጽ ለማድረግ ያግዛል።
ጥናቱ የአከራዮችን ተገቢ ገቢ ከወቅታዊ የኢኮኖሚ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የሚያረጋግጥ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ተከራዮችም ከገቢያቸው ጋር የተመጣጠነ ኪራይ እንዲከፍሉ እና የተረጋጋ የኢኮኖሚ ኑሮ እንዲመሩ እንደሚያስችል ተገልጿል።
እንዲሁም ጥናቱ የቤት ኪራይ ገበያውን ጤናማና ሊተነበይ በሚችል መልኩ በማደራጀት፣ በአከራይና ተከራይ መካከል ያለውን የእምነት ክፍተት ለመቀነስ እንዲሁም የሕገ-ወጥ ደላሎችን ጣልቃ ገብነት ለመግታት እንደሚረዳ ተጠቁሟል።
ጥናቱ በአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ በ2019 በጀት ዓመት በተግባር እንደሚውል ተገልጿል።
@Seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.