#FastMereja I የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው የወንጀል ችሎት የ6ወር ነፍስጡር የሆነችው ባለቤቱን የገ ደለው ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል።
ጎፋ ዞን በላሃ ከተማ አስተደዳር ሀብት-ምንጭ ቀበሌ ክልል ውስጥ ነዋሪ የሆነው ተከሳሽ አቶ ጀማል ሁሴን የተባለው ግለሰብ በሞት እንዲቀጣ የተወሰነበት ከባለቤቱ ጋር በነበረ የፍትሐብሔር ክስ ክርክር ቂም ይዞ በስለት የተለያየ የሰውነት ክፍሏን በመውጋት በአሰቃቂ ሕይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉ በማስረጃ በመረጋገጡ ነው።
የለሃ ከተማ ፖሊስ ወንጀል ፈጽሟል ተብሎ የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ያጣራ ሲሆን የምርመራ መዝገብን በሰውና በህክምና አደራጅቶ ለዞኑ አቃቤ ህግ ልኳል።
የጎፋ ዞን ዐቃቤ_ሕግ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ተደግፎ ከፖሊስ የደረሰው መዝገብ በማየት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወ.ሕ.አንቀጽ 539(1) (ሀ)ን በመጥቀስ ክስ መስርቶበታል ።
ክሱ የቀረበለት የጎፋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ዐቃቤ-ሕግ ያቀረባቸው ማስረጃዎች እንደ ክሱ ጭብጥ ከጥርጣሬ በላይ ያስረዱ ስለሆነ ተከሳሽ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር እንዲከላከል ብይን የሰጠ ሲሆን ተከሳሽም የመከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ ተከሳሽ በተከሰሰበት ድንጋጌ ስር ጥፋተኛ በማለት ፍርድ ሰጥቷል።
በመቀጠልም ፍ/ቤቱ የግራ ቀኙን የቅጣት አስተያየት ተቀብሎ ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ/ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ጀማል ሁሴን በሞት እንዲቀጣ ወስኗል::
Source: FastMereja









No comments yet.