🌱🌱
—————————————–
#Ethiopia | በዚህ ምድር ላይ እንደ ወላጅ የገዛ ፍሬህን፣ ገና የህይወትን ጣዕም ያላወቀውን የ3 አመት ተኩል ህጻን ልጅህን በአይንህ ፊት በህመም ሲያለቅስ እና ሲሰቃይ እያዩ ምንም ማድረግ አለመቻል የሚሰማውን የህሊና እሳት እና የልብ ስብራት የሚገልጽ ቃል የለም።
የእኔ አምሳል፣ የምወደው ልጄ ፀጋዘዓብ በአሁኑ ሰዓት በአስከፊው የአጥንት ካንሰር (Bone Cancer) ህመም ውስጥ ሆኖ ሌሊትና ቀን በስቃይ ይጮኻል። እሱን ወደ ጤንነቱ ለመመለስ እና ህይወቱን ለማዳን በአንድ ወር ውስጥ በውጭ ሀገር የሚደረግ የአጥንት ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል። ነገር ግን ለዚህ ህክምና የሚጠይቀው ወጪ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ነው። ይህ የገንዘብ መጠን የእኔን አቅም ጥሶ የልጄን የህይወት በር እየዘጋው ነው።
የህክምና ባለሙያ (ሀኪም) መሆኔ ደግሞ ዛሬ በእኔ ላይ ሌላ ትልቅ ጠባሳ ጥሏል። ሁልጊዜ የሌሎችን ወገኖቼ ልጆች እና ወገኖቼን ህይወት ለመታደግ የምተጋው፣ ዛሬ የገዛ ልጄን ስቃይ እያየሁ፣ ህይወቱን ማዳን አለመቻሌ ውስጤን በቁም ነገር ያሳርረዋል።
የጊዜው መቆጠር፣ በእያንዳንዱ ሰከንድ ልጄን ወደ ሞት አፋፍ እየገፋው ነው። ለልጄ ተስፋው እናንተ ናችሁ።
እናንተ ትንሽ የምትሏት እርዳታ ለልጄ ለፀጋዘዓብ ዳግም የመኖር ተስፋ ናት። የጨቅላውን ልጅ እምባ አብሰን፣ ከዚህ ከባድ ስቃይ አብረን እንታደገው።
ፈጣሪ የደግነት እጃችሁን ይባርክ! 🙏
የሮም ጌታቸው
CBE – 1000149557982
Abay – 2091011011819814
Awash : 013201344371300
Tele birr: 0910119336
GoFundMe: https://www.gofundme.com/f/help-tsegabe-fight-cancer?lang=en_US&ts=1780047340


Source: GetuTemesgen









No comments yet.