42ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን እሁድ በሀዋሳ ይካሄዳል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 42ኛውን የሻምበል አበበ ቢቂላ ማራቶን ውድድር ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁን አስታውቋል። ውድድሩ የፊታችን እሁድ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ይካሄዳል።

የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ የውድድር ባለሙያ አቶ ብስራት ለጥይበሉ እና የኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ አቶ መሐሪ ነጋሽ በሰጡት መግለጫ፣ ውድድሩ ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለክልሎች፣ ለከተማ አስተዳደሮች፣ ለክለቦች እና ለግል የማራቶን ሯጮች የውድድር ዕድል ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም አትሌቶችን በሽልማት በማበረታታት የማራቶን ውድድርን ለማጠናከር የታለመ መሆኑን አስረድተዋል።

በዘንድሮው ውድድር 74 ሴቶች እና 249 ወንዶች በድምሩ 323 አትሌቶች ይሳተፋሉ። በሴቶችና በወንዶች ምድብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ለሚያጠናቅቁ አሸናፊዎች ከሜዳሊያ በተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውድድሩን ከሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ሰኔ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. በሀዋሳ ከተማ ያካሂዳል።

#Ethiopia #Hawassa #GetuTemesgen





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: