መምህር ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕ)፤

- Advertisement -
Sidebar AD

የ “የዓመቱ ምርጥ የሁነት አስተዳዳሪ”
(Best Event Manager of the Year)

#Ethiopia | በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል በተከናወኑ የተሳኩ መርሃ ግብሮች መሠረት፣ የዩኒቨርሲቲው መምህርና የባህል ማዕከል ዋና ዳይሬክተር መምህር ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕ) የ”የዓመቱ ምርጥ የሁነት አስተዳዳሪ (Best Event Manager of the Year)” እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል የሚል ግምገማ እየተሰጠ ነው።

በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 60 ያህል ሳምንታዊ ታላላቅ ሁነቶችን በማዘጋጀትና ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች ታዋቂ እንግዶችን በመጋበዝ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ጠቃሚ የዕውቀት ልውውጥ እንዲኖር በማድረጋቸው በርካቶች አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

እንዲሁም ሳምንታዊው Hello Ethiopia በFM Addis 97.1 ፕሮግራም እነዚህን ሁነቶች በተከታታይ በመዘገብ ለሕዝብ አድርሷል።

መምህር ተስፋዬ እሸቱ ለዚህ እውቅና የሚያበቁባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች

የሁነት ማቀድና ማስተዳደር ላይ ያላቸው ከፍተኛ ብቃት።

በመድረኮች ላይ ፈጠራ የተሞሉ ሀሳቦችን በማስተዋወቅ ከተለያዩ ዘርፎች ስኬታማ ባለሙያዎች ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ ማድረግ።

ሙያዊ ግንኙነቶቻቸውን ለተቋሙ ጥቅም በብቃት መጠቀም።

የዩኒቨርሲቲውን ማኅበረሰብ ከውጭ ካሉ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በቅርብ ግንኙነት ማስተሳሰር።

የአጋር ድርጅቶችን ተሳትፎ በማሳደግ ሁነቶቹ በቀጣይነት እንዲከናወኑ ማድረግ።

ተማሪዎች ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር ሰፊ የሕይወት እይታ እንዲያገኙ አስተዋጽኦ ማድረግ።

ባለሙያዎችን በማስተባበር ሁነቶችን በብቃት መምራት።

የበጀት ውስንነት ቢኖርም በፈጠራና በጥሩ አመራር ሁነቶቹን በስኬት ማስቀጠል።

ሙያውን በክብር መያዝና ለሌሎችም ክብር እንዲኖረው መስራት።

በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች መምህር ተስፋዬ እሸቱ “የዓመቱ ምርጥ የሁነት አስተዳዳሪ” ተብለው እንዲጠሩ የሚያስችል አፈጻጸም አሳይተዋል።

እንዲህ ያለ መሪ በአጠገባቸው ያላቸው ተማሪዎችም በእርግጥ እድለኞች ናቸው።

ማናዬ እውነቱ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2