ሴኔጋል ኢራቅን 5-0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋውን አጠናከረ!

- Advertisement -
Sidebar AD

🇸🇳

#FIFA | ሴኔጋል በተደረገው ጨዋታ ኢራቅን 5-0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ በምድቡ ውስጥ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ እድሉን አጠናክሯል።

የሴኔጋልን የድል ጎሎች ሃማዱ ዲያራ (4′)፣ ኢብራሂማ ሳር (56′)፣ ፓፕ ጉዬ (59′ እና 71′) እንዲሁም ኢላይማን ንዲያዬ (82′) አስቆጥረዋል።

ኢራቅ ደግሞ በ13ኛው ደቂቃ ተከላካዩ ረዋንድ ሱላካ ቀይ ካርድ በማየቱ ከጨዋታው ተሰናብቶ ቀሪውን ጊዜ በ10 ተጫዋቾች ለመጫወት ተገዷል።

ይህ ድል ለሴኔጋል በምድቡ ውስጥ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን፣ ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ተስፋውን በእጅጉ አሳድጎታል።


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1