በሳውዲ አረቢያ በ12 ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ፍርድ ተፈጸመ።ሌሎች 63 ዜጎችም በሞት ስጋት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።እንደ መብት …

- Advertisement -
Sidebar AD
በሳውዲ አረቢያ በ12 ኢትዮጵያውያን ላይ የሞት ፍርድ ተፈጸመ።
ሌሎች 63 ዜጎችም በሞት ስጋት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
እንደ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ገለጻ፣ በደቡብ ምዕራብ ሳውዲ አረቢያ በሚገኘው ከሚስ ሙሻይት ማቆያ ማዕከል ውስጥ በአንድ ክፍል ብቻ የታሰሩ 63 ኢትዮጵያውያን ከዕፅ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ብቻ በማንኛውም ሰዓት የሞት ፍርድ ሊፈጸምባቸው እንደሚችል በከፍተኛ ስጋት ገልጿል።
ሳውዲ አረቢያ በዘንድሮው ዓመት ብቻ የሞት ፍርድ የፈጸመችባቸው ሰዎች ቁጥር 100 መድረሳቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ በሳውዲ ባለሥልጣናት የሞት ፍርድ ከተፈጸመባቸው 100 ሰዎች መካከል 12ቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው።
ቀሪዎቹ 48 ሳውዲውያን፣ 7 ፓኪስታናውያን፣ 6 ሱዳናውያን፣ 4 የመናውያን እና 4 ሶርያውያን መሆናቸውን የፈረንሳይ የዜና አገልግሎት  ከመንግሥት መግለጫዎች በመነሳት ዘግቧል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: