የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እናት አረፉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እናት ወ/ሮ አዳነሽ በርሄ በ97 ዓመታቸው ማረፋቸውን የአገሪቱ ማስታወቂያ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ከኤርትራ ነጻነት አንስቶ ከ35 ዓመታት በላይ በብቸኝነት ኤርትራን እየመሩ ያሉት የ80 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ እናት ያረፉት ሰኞ ዕለት ነበር።

ረቡዕ ሰኔ 17/2018 ዓ. ም. አሥመራ አቅራቢያ በሚገኘው የትውልድ ስፍራቸው በተፈጸመው ቀብር ሥነ ሥርዓት ላይ ፕሬዝዳንት ኢሳያስን ጨምሮ ቤተሰቦች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ከፍተኛ ባለሥልጣናት መገኘታቸውን የማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ አመለክቷል።

የፕሬዝዳንት ኢሳያስ እና ወ/ሮ አዳነሽ በርሄ ከአቶ አፈወርቂ አብርሃ ጋር በትዳር በቆዩባቸው ጊዜያት 14 ልጆችን ያፈሩ ሲሆን፣ ዘጠኙ ለነጻነት በተካሄደው እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳተፊ እንደነበሩ ይነገራል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ ወ/ሮ አዳነሽ በኤርትራ ውስጥ ጦርነቱ በሚካሄድበት ወቅት ወደ አሜሪካ ሄደው የኖሩ ሲሆን፣ ኤርትራ ነጻ አገር ስትሆን ተመልሰው እስከ ኅልፈታቸው ድረስ በኤርትራ ኖረዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2