የታዋቂው ፖለቲከኛ አንዱዓለም አራጌ መጽሐፍ በሀገር ውስጥ ታትሞ ለገበያ ቀረበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የአንዱዓለም አራጌ፣ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› የተሠኘው አዲስ መጽሐፍ፤ በሁለት ክፍሎች፣ በአምስት ምዕራፍ፣ በ500 ገጽ ተሠናድቶ በ850 ብር ለሀገር ውስጥ ገበያ ቀርቧል፡፡

‹‹ብዕርና ባሩድ››፣ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ስንክሳር በጥልቀት የሚዳስስ፣ በኢትዮጵያ የሰባ ዓመታት ፖለቲካ ውስጥ፣ በአንድ ወይንም በሌላ መልኩ ጉልህ ሚና የተጫወቱ፣ የአሥራ ስምንት ጉምቱ ፖለቲከኞችን ሃሳብ ‹‹ከፈረሱ አፍ›› በሚል ክፍል ስር በማራኪ ኹኔታ ቀርቦበታል፡፡

ከወራት በፊት በጀርመን አገር ፍራንክፈርት ከተማ ታትሞ በዚያው ተመርቆ የዘመኑን የሕትመት ብርሃን ለማየት የበቃው ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ፤ በአሜሪካን አገርም ታትሞ በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በዋሽንግተን ዲሲ፣ ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ቦስተን፣ አትላንታ፣ ኦክላንድ ቴክሳስ፣ ሲያትል፤ ዴንቨር፣ ላስቬጋስ እንዲሁም በካናዳ- ቶሮንቶ በሽያጭ ላይ ይገኛል፡፡

‹‹ከዚህ በፊት ሁሉም በየፊናው ምልከታውን በመሠለው መንገድ ያቀርባል እንጂ፣ እንደ ‹‹ብዕርና ባሩድ›› መጽሐፍ፣ የበርካታ የፖለቲካ ልሂቃንን ክርክር በአንድ ጥራዝ ስር ያቀረበ ብሎም ያከራከረ ድርሳን የለም›› ሲሉ በውጭ አገራት የሚገኙ የሥነ-ጽሑፍ ሃያሲያን በምረቃው ዕለት ገልጸዋል፡፡

‹‹ብዕርና ባሩድ›› የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅጡ ለመረዳት ለሚሹ፣ ለተመራማሪዎችና ለሀገራቸው የፖለቲካ ችግር መፍትሄ ለሚሹ ሁሉ፤ በጥንቃቄና በሚዛናዊነት ደፍ ላይ የቆመ ድንቅ መጽሐፍ ነው ብለዋል፡፡

‹‹ብዕርና ባሩድ›› በአውሮፓ፡- በፍራንክፈርት፣ በርሊን፣ ሎንዶን፣ ስቶኮልም፣ ኦስሎ፣ ብራስልስ እና ስዊዘርላንድ በሽያጭ ላይ ይገኛል፡፡

በአማዞንም፣ በሕትመት- በኪንድል (Paparback) እና በኢ-ቡክ (e-book) ታትሞ ለአንባቢዎች እነኾ ቀርቧል፡-

https://a.co/d/03bbV8Zy

አሁን ደግሞ፡ ለሀገር ውስጥ አንባቢዎች በጃዕፈር እና ሌሎች መጽሐፍ መደብሮች እንዲሁም በአዟሪዎች እጅ በገበያ ላይ ቀርቧል፡፡


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: