ውሻዉን ያልገደለ ግለሰብ በ50,000 ብር እና በእስራት እንዲቀጣ ታወጀ !በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሆሳና ከተማ እያንዳንዱ …

- Advertisement -
Sidebar AD
ውሻዉን ያልገደለ ግለሰብ በ50,000 ብር እና በእስራት እንዲቀጣ ታወጀ !
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሆሳና ከተማ እያንዳንዱ ግለሰብ በቤቱ ያለዉን ዉሻ አውጥቶ እንዲገድል በታወጀው መሰረት ዉሻ ያላቸው ግለሰቦች ….
ዉሻቸውን ገመድ በማጥለቅ በቀንጨት ላይ በማንጠልጠል ዉሾችን እያነቁ እየገደሉ መሆኑን በትናንትናው ዕለት ግዮን ማለዳ ዘግቦ ነበር።
በሆሳእና ከተማ ከሰሞኑ በውሻ ምክንያት በሽታ ተከስቷል የተባለ ሲሆን ይህ የውሻ ግድያ ዘመቻ የተጀመረው አንድ ውሻ የ13 አመት ልጅ ነክሳው ከሞተ በኋላ መሆኑን ታውቋል።
ቪዲዮዎች Ghion Maleda የቴሌግራም ቻናል እንደምታዩት የራሳቸው ባለቤት ያላቸውና ክትባት የተሰጣቸው ውሾችን ጨምሮ በእጅግ አሰቃቂ ሁኔታ በመንጋ ውሾችን እያስጮሁ ዛፍ ላይ በማ- ነቅ የገደሏቸው ።
በኮምቦልቻ ከተማ የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) ከባድ የሕዝብ ጤና ስጋት መሆኑን ሪፖርቶች ቢወጡም መሰል ከሰባዊነት ያፈነገጠ ተግባር በፍጹም አልተደረገም ነበር ።
በሆሳና ከተማ በጣም የሚያሳስበው፣ አንዳንድ ሕፃናት በእነዚህ ድርጊቶች ውስጥ ተሳትፈዋል በቪዲዮዎች ተመልክተናል ።ጉዳዩ የእንስሳት ደህንነት ብቻ ሳይሆን ለሚቀጥለው ትውልድ ምን ዓይነት እሴቶችን እያስተላለፍን እንዳለን የሚያስጠይቅ ነው። ርኅራኄ ይማራል፤ ጭካኔም እንዲሁ ይማራል።
የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) ከባድ የሕዝብ ጤና ጉዳይ ነው፣ መቆጣጠር ያስፈልጋል። ሆኖም የሳይንስ ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት ችግሩን በዘላቂነት የሚቀንሱት…
ሰብዓዊና ውጤታማ መንገዶች እንደ የጅምላ ክትባት፣ የውሾች ማምከን፣ ለሕዝብ ግንዛቤ መስጠት እና ኃላፊነት ያለው የእንስሳት አስተዳደር ናቸው፤ ጭካኔ እና ግፍ ግን መፍትሔ አይደሉም።via Ghion maleda
@Seledadotio
@Seledadotio


Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: