በሀገራችን ያሉ አንጋፋ እና ወጣት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በባህርዳር ዩንቨርስቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል የሚገኙ ተማሪዎችን ያስመረቁት ዛሬ በዩንቨርስቲው የ2018 ዓ. ም ተመራቂ ተማሪዎች በተመረቁበት የባህርዳር ዩንቨርስቲ በመገኘት ነው።
ባለሙያዎቹ በምረቃ ስነስርዓት ላይ ሲታደሙ ከአጠቃላይ ተመራቂዎች ፣የተመራቂ ቤተሰቦች እና የዩንቨርስቲው መምህራንና ግቢው ማህበረሰብ ሞቅ ያለ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የኪነጥበብ ባለሙያዎቹ በልዩነት ዛሬ በተመረቁት የቴአትር ጥበባት ተማሪዎች መሐከል መገኘታቸው ደግሞ ወጣቶች በተሻሉ ስራዎች ወደ ጥበብ መንደር እንዲቀላቀሉ ትልቅ የሞራል ስንቅ እንደሚሆናቸው ታምኗል።
ከዚህም ባሻገር በጥበብ ለሀገርና ለህዝብ ማገልገል የሚያስገኘውን ክብርና አቀባበል የዘንድሮ ተመራቂዎች ማየት መቻላቸው ወደ ስራ እና ማህበረሰቡ ዘልቀው ለሚገቡት የዛሬ ተመራቂዎች ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥራል ተብሏል። የኪነጥበብ ባለሙያዎችም በዚህ መሰል ስነስርዓት ላይ በባህርዳር ዩንቨርስቲ በመገኘታቸው ከፍ ያለ ደስታ እንደፈጠረላቸውና የዘንድሮው ተመራቂዎችም ይህንን እድል ማግኘታቸው ከፍ ያለ መነሳሳትን ሊፈጥር እንደሚችል ተናግረዋል ።
በአርቲስት ወይንሸት አበጀ እና አርቲስት አሸናፊ ማህሌት አስተባባሪነት እና በባህርዳር ዩንቨርስቲ ጋባዥነት በከተማዋ የታደሙት የኪነጥበብ ባለሙያዎች በመሰል ለሀገርና ለወገን በሚጠቅሙ ተግባራት ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ።



Source: FastMereja









No comments yet.