በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ስደተኞች ሀገሪቱን ጥለው እየሸሹ ነው!
እንደ አልጀዚራ (Al Jazeera) የዜና ዘገባ ከሆነ በደቡብ አፍሪካ በተቀሰቀሰው ከፍተኛ የውጭ ዜጎች ጥላቻ (Xenophobia) እና ጥቃት ምክንያት፣ እንዲሁም June 30 ሊደረግ ከታቀደው መጠነ-ሰፊ ፀረ-ስደተኞች ሰልፍ አስቀድሞ በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ስደተኞች ሀገሪቱን በከፍተኛ ስጋት እየለቀቁ ይገኛሉ።
እንደ ማላዊ፣ ዚምባብዌ፣ ናይጄሪያ፣ ጋና እና ሞዛምቢክ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት መንግስታት ዜጎቻቸውን በፈቃደኝነት ወደ ሀገራቸው ለመመለስ (Repatriation) የአውቶቡስ እና የሎጂስቲክስ ዝግጅቶችን እያደረጉ ሲሆን፣ በርካታ ስደተኞችም ጥበቃ ፍለጋ በየሀገራቱ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች ደጅ ላይ ተሰባስበው ይገኛሉ።
ይህ የጊዜ ገደብ መጀመሪያ ላይ የደቡብ አፍሪካን መንግስት አርማ ተጠቅሞ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት በተሰራጨ የሀሰት (AI-generated) ፖስተር የተነሳ የመጣ ቢሆንም፣ “ማርች ኤንድ ማርች” (March and March) የተባሉ የፀረ-ስደተኛ አደረጃጀቶች እና ቡድኖች ግን ህገ-ወጥ ስደተኞች በሙሉ እስከ June 30 ድረስ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ በማስገደድ የራሳቸውን መጠነ-ሰፊ ዘመቻ ከፍተዋል።
ምንም እንኳን የተሰጠው የጊዜ ገደብ ህጋዊ ባይሆንም፣ በተለያዩ ከተሞች (ለምሳሌ በሞሰል ቤይ) በስደተኞች መኖሪያ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል፣ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ ንብረቶች ተዘርፈዋል እንዲሁም የሰው ህይወት ጠፍቷል።
ጋና በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿን በልዩ የአየር በረራ የመለሰች ሲሆን፣ ማላዊ ከ5,000 በላይ ሰዎችን በባስ ለማጓጓዝ እየሰራች ነው።
ናይጄሪያ እና ሞዛምቢክም በተመሳሳይ ሁኔታ ዜጎቻቸውን የማስወጣት ስራ ላይ ናቸው።
ጉርሻ
@Seledadotio

No comments yet.