#Ethiopia | ናይሮቢ በሚገኘው ጆሞ ኬንያታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ረቡዕ ዕለት በተፈጸመ ድንገተኛ ክስተት ኬንያ ሐሰተኛ ፓስፖርት ይዘዋል በሚል የሶማሊያውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጂብሪል አብዲራሺድ ሐጂን ወደ ሀገራቸው አባረረች።
ባለሥልጣናቱ ጥያቄ በሰነዘሩባቸው ወቅት የኬንያ የጉዞ ፓስፖርት እንዳላቸው ቢያምኑም ሰነዱን ማቅረብ የሚችሉት በፍርድ ቤት ፊት ብቻ መሆኑን በመግለጽ አሳልፈው ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሞቃዲሹ የተነሱት በሶማሊያ ዲፕሎማቲክ ፓስፖርት እና በሕጋዊ ቪዛ ቢሆንም የኬንያ የደኅንነት አካላት በቪአይፒ ማረፊያ ክፍል ውስጥ ካቆዩዋቸው በኋላ ሐሙስ ጠዋት በዳሎ አየር መንገድ በረራ ወደ መነጩበት ሞቃዲሹ መልሰዋቸዋል።
ይህ ክስተት በሙስና ሰበብ ሶማሊያውያን የኬንያ ሰነዶችን የማጭበርበር ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመጣበት ወቅት የተሰማ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ግን ከኬንያም ሆነ ከሶማሊያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.