#Ethiopia | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የሥነ-ጥበብ ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ “Ethiopian Visual Arts Global Network” የተሰኘ የመረጃ ቋት በማደራጀት ላይ መሆኑን ገልጿል።
ይህ መድረክ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ሰዓሊያንና የሥነ-ጥበብ ባለሙያዎች እርስ በርሳቸው እንዲገናኙ፣ መረጃ እንዲለዋወጡ እና የፈጠራ ሥራዎቻቸውን በዓለም አቀፍ መድረክ እንዲያስተዋውቁ የሚያግዝ እንደሆነ ተገልጿል።
በዚህም የትምህርት ቤቱ ምሩቃን፣ በሌሎች ተቋማት የተማሩ እንዲሁም በልምድ የዳበሩ ሰዓሊያን በሙሉ በተዘጋጀው ዲጂታል ቅጽ በመመዝገብ የዚህ ዓለም አቀፍ መረብ አካል እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል።
ተሳታፊዎች ማንነታቸውን እና የሙያ ልምዳቸውን የሚገልጽ መረጃ በመሙላት የኢትዮጵያን ሥነ-ጥበብ በዓለም መድረክ ላይ በጋራ እንዲያደምቁ የአለ የሥነ-ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ጋብዟል።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.