በርካታ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን በዛሬው እለት ያስመርቃሉ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#Ethiopia | ​ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በመላ ኢትዮጵያ የሚገኙ ከ25 በላይ የሚሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለዓመታት ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ያስመርቃሉ።

‎በዚህ የተማሪዎች ምረቃ በዓል ዕለት የአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ የባሕርዳር፣ የጅማ እና የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የድካማቸውን ፍሬ ለመቅጠፍ ጋውን ይለብሳሉ።

‎በዚሁ ዕለት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙት የዲላ፣ ቡሌ ሆራ፣ ጅንካ፣ ሚዛን-ቴፒ፣ አርባ ምንጭ፣ ዋቸሞ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ቦንጋ እና መቱ ዩኒቨርሲቲዎችም የምረቃ ስነ-ሥርዓታቸውን በደመቀ ሁኔታ ለማካሄድ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል።

‎​በተመሳሳይ መልኩ በሰሜኑና በምሥራቁ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙት የደባርቅ፣ ሰላሌ፣ አክሱም፣ ወልድያ እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም የቀብሪደሃር፣ ድሬዳዋ፣ ኦዳ ቡልቱም እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች ማህበረሰብ ከተመራቂ ቤተሰቦች ጋር በመሆን ደስታቸውን ለመካፈል በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

‎በተጨማሪም በምዕራብና ተያያዥ ክልሎች የሚገኙት የጋምቤላ፣ ወራቤ፣ አሶሳ፣ ደምቢ ዶሎ እና ቦረና ዩኒቨርሲቲዎች ከአዲስ አበባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመሆን በዛሬው ዕለት አዳዲስ አምራች ኃይሎችን ወደ ሥራው ዓለም ለመቀላቀል ሽርጉድ እያሉ ነው።

‎ከባሳለፍነው ሐሙስ ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ጎንደር ፣ እንጅባራ ፣ ወለጋ ፣ ደብረ ታቦር ፣ ወልቂጤ ፣ራያ ፣ ወሎ ዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎቻቸውን አስመርቀዋል።

ጌትነት ተመስገን
‌‎Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

‎#getutemesgen #getu #ጌጡ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1