በአዶላ ከተማ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ወርቅ ለማግኘት መሬቱን እየቆፈረ ነው።”በማህበራዊ ሚዲያ እጅግ መነጋገሪ ከሆኑት እንድ የሆነ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በአዶላ ከተማ ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ወርቅ ለማግኘት መሬቱን እየቆፈረ ነው።”
በማህበራዊ ሚዲያ እጅግ መነጋገሪ ከሆኑት እንድ የሆነው የአዶላ ህዝብ በመናኽሪያ ጭምር እና በየቦታው ወርቅ ና ማዕድን ፍለግ መሬቱን እየቆፈ ነው፡፡
በኦሮሚያ ክልል አዶላ በተባለችው ከተማ በአሁኑ ወቅት እጅግ ያልተለመደ እና አነጋጋሪ ክስተት እየታየ ይገኛል።
በከተማዋ አሸዋማ እና አፈራማ አካባቢዎች ውስጥ ወርቅ እንዲሁም የከበሩ ድንጋዮች በብዛት ተገኝተዋል የሚል ወሬ በስፋት መሰራጨቱን ተከትሎ፣ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ አካባቢውን ወርሯታል።
ይህንን ተከትሎ ህፃናት፣ ወጣቶች እንዲሁም አዛውንቶች ሳይቀሩ በከተማዋ በተለያዩ ስፍራዎች፣ በመናኽሪያ አካባቢ ጭምር አፈሩን ሲቆፍሩ ውለው እያደሩ መሆናቸውን ከተለያዩ ምስሎችና ቪዲዮዎች ለመረዳት ተችሏል።
ነዋሪዎቹ በቡድን በመሆን ፍለጋቸውን በከፍተኛ ጉጉት አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፣ አንዳንዶች በቁፋሮ ያገኟቸውን የሚያንፀባርቁ፣ ትላልቅ እና የከበሩ ድንጋይ የሚመስሉ ማዕድናት በሞባይል ስልክ ብርሃን እያበሩ ሲያሳዩ ይታያል።
ይህ በድንገት የተቀሰቀሰው ህዝባዊ የማዕድን ፍለጋ ግርግር በከተማዋ የዕለት ተዕለት ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ የራሱን ትልቅ ጫና እያሳደረ ይገኛል።gursha
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: