በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው ላሊዛግ ጤና ሳይንስና ቢዝነስ ኮሌጅ ለ6ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን 540 ተማሪዎችን አስመረቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ኮሌጁ በዛሬው ዕለት ካሴመረቃቸው ተማሪዎች መካከል 320 ሴቶች ናቸው።

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ለተመራቂዎች መልዕክት ያስተላለፉት የአዊ ብሄ/አስ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ ደስታው አለሙ፥ተመራቂዎች ብዙ ፈተናዎችን ተቋቁማችሁ እዚህ በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ብለዋል።

የዛሬ ተመራቂዎች በኮሌጅ ቆይታችው የቀሰሙትን እውቀት ወደ ተግባር በመቀየር ለኢትዮጵያ ሰላምና እድገት የመፍትሄ አካል ለመሆን መትጋት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።

በምረቃ መርሃ ግብሩ የተገኙት የኮሌጁ ባለቤት እና ስራአስኪያጅ ቢምረው አድማሱ፥ትምህርት የአንድ ሀገር ዕጣ ፈንታ የሚቀይር ሀያል መሳሪያ ነው።

ዛሬ በተለያየ ሙያ ዘርፍ የተመረቃችሁ ተማሪዎች የወደፊት የሀገራችን ውድ “ሀብቶቻችን ናችሁ” ብለዋል።

በአገኛችሁት እውቀት በታማኝነት፣በትጋት እና በሀገር ፍቅር በማገልገል ለሀገራችሁ ብርሃን ሁኑ ሲሉም መክረዋል።

ኮሌጁ ከተመሠረተ 2011ዓ.ም ጀምሮ የዛሬዎቹን ጨምሮ ከ6ሽህ 700 በላይ ተማሪዎችን በማስመረቅ ለሀገራችን የሰው ሀይል ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማድረጉን ስራአስኪያጁ ተናግረዋል።

ኮሌጁ በርካታ ማኅበረሰብ አቀፍ ሥራዎችን እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰው፣ ይህን ማስቀጠል የሁሉም የኮሌጁ አካል የሆኑ ተማሪዎች እና ሠራተኞች ኃላፊነት መሆኑን አክለዋል።

ከተመራቂዎች መካከል፣ ኤልያስ ሀይሉ በቢዝነስ ማኔጅመንት እጅግ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ የኮሌጁ የ2018 የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: