የ‘ዶፒንግ’ ጉዳዮች የፍርድ ሂደት ከ2 ዓመት በላይ መዘግየቱ እንዳሳሰበው የፀረ-አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን ጠቆመ

- Advertisement -
Sidebar AD

አቤቱታ የቀረበባቸው ከጸረ-አበረታች መድኃኒት (ዶፒንግ) ጋር የተያያዙ ክሶች በምርመራ ሂደት ከሁለት ዓመት በላይ መውሰዳቸው የፍትሕ ሂደቱን እያጓተተ እንደሆነ የጸረ-አበረታች ቅመሞች ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የባለሥልጣኑ የሕግ አፈጻጸም እና ትግበራ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ መኮንን ለአሐዱ ሬዲዮ እንደገለጹት፤ ያለ በቂ እና አሳማኝ ምክንያት የሚዘጉ የዶፒንግ ክሶች አሉ፡፡

“ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጠንከር ያለ ጥፋት በፈጸሙ ጥፋተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ከመውሰድ ባሻገር ክትትል እያደረገ፤ የሕግ ሂደቱን ተከትሎ ይግባኝ በመጠየቅ ጥፋተኞችን ለማስቀጣት ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል” ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በአጥፊዎች ላይ በርካታ ክሶች ተመስርተው ለፍርድ ቤት መቅረባቸውን አስታውሰው፤ እስካሁን በፍርድ ቤት የመጨረሻ ውሳኔ አግኝቶ እልባት የተሰጠው አንድም ጉዳይ አለመኖሩ “የጉዳዩን አሳሳቢነት ይገልጻል” ብለዋል፡፡

ባለሥልጣኑ በአትሌቶች እና ድጋፍ ሰጪ ባለሙያዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃዎችን በበቂ ሁኔታ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።

ተቋሙ ከዚህ ቀደም በ5 የሕክምና ተቋማት እና በሃያ አትሌቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን ለአሐዱ ሬዲዮ መግለጹ ይታወሳል።

#አሐዱ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1