“የሕይወት መንገድ” ለንባብ በቃ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የመጀመሪያው የጉራጊኛ ረጅም ልቦለድ ደራሲ 16ኛው መጽሐፋቸውን ለንባብ አብቅተዋል።

የመጀመሪያው የጉራጊኛ ረጅም ልቦለድ “የጫሙት ሽካ”ን በመጻፍ በኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ የማይረሳ አሻራ ያኖሩት አንጋፋው ደራሲ አጋዝ ገብረኢየሱስ ኃይለማርያም “የሕይወት መንገድ” የተሰኘውን 16ኛው መጽሐፋቸው ዛሬ ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በብሔራዊ ቴአትር አዳራሽ አስመርቀዋል።

ደራሲው በጉራጊኛ፣ በአማርኛና በእንግሊዝኛ 16 መጽሐፍትን የጻፉ ሲሆን፣ ለጉራጌ ቋንቋና ባህል ጥበቃ፣ አንድነትና እድገት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

ከዚህም ባሻገር የጉራጌ ሕዝብ ራስ አገዝ ልማት ድርጅት (ጉህራልድ) መሥራች በመሆን “በማኅበረሰብ ልማት” ዘርፍ ጉልህ ይታወሳሉ።

አጋዝ ገብረየሱስ በድርሰት ሥራ ላበረከቱት ልዩ አስተዋፅኦ ዕውቅና ከኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ተበርክቶላቸዋል።

እርሳቸውም መጻሕፍታቸውን ሲያሳትሙ ለትልቅ ማህበረሰባዊ ዓላማ እንደነበር በማስታወስ በ97 አመታቸው እንዲህ አይነት እውቅናና ክብር በማግኘታቸው የተሰማቸውን ልዩ ደስታ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ደራሲያን ማህበር ፕሬዝዳንት ደራሲ አበረ አዳሙ አጋዝ ገብረየሱስ የፅናት ተምሳሌት መሆናቸውን ያስረዱ ሲሆን “የደራሲያን ማህበርም እውቅና በመስጠቱ ኩራት ይሰማዋል” ብለዋል።

የጉራጌ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ሀላፊና በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ደሳለኝ ገብሬ በመርሀ ግብሩ ባደረጉት ንግግር አጋዝ ገብረየሱስ ለአዲሱ ትውልድ አርአያ የሚሆኑ በተለይም በድርሰቱ መስክ ትልቅ አሻራ ያኖሩ በመሆናቸው እናከብራቸዋለን ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ደራሲ ገብረየሱስ በሁለቱ የጉራጌ ዞኖች ለሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚውል 1000 መጽሃፍትን በልገሳ ያበረከቱ ሲሆን የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወልዴ መጻህፍቱን ለማሰራጨት ሀላፊነት ወስደዋል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር ካሚል ኑረዲን በመድረኩ የመጽሐፍ ዳሰሳ ያቀረቡ ሲሆን የደራሲው የበኩር ልጅ ኢትዮጵያ ገብረየሱስ የ“እንኳን ደስ አልዎ” መልዕክትና የቤተሰባዊ ምስክርነት ንግግር አድርገዋል።

መፅሐፉ በደራሲ ብርሀነ ዓለሙ የተሰናዳ ሲሆን የምረቃ ስነ-ስርዓቱን ተወዳጅ ሚድያና ኮሙኒኬሽን ከሶዶ ለማ ሚዲያ ጋር በመሆን አዘጋጅተውታል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#የሕይወትመንገድ
#ደራሲአጋዝገብረየሱስሀይለማርያም
#ጌጡተመስገን #ሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemsgen #Mediacommunication






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: