ሐረር ቢራ፣ ሳቃችንን እየመነዘረ ከጓደኞቻችንና ከምንወዳቸው ጋር የሚያገናኘንን አዲስ «ሳቅፔ» (SAQPay) የተሰኘ መተግበሪያ ይዞልን ከች ብሏል!
ለመሆኑ የማህበራዊ ህይወታችን እውነተኛ ዋጋ በገንዘብ ልውውጥ ብቻ ይለካል እንዴ? ከወዳጆቻችን ጋር የምናሳልፈው ያ ደስ የሚል ጊዜ እንጂ! ይህንን እውነት መነሻ በማድረግ፣ ሐረር ሳቃችንን በቀጥታ
ልንመነዝረው ወደምንችለው ጥቅም የሚቀይር አዲስ ፈጠራ ይዞ መጥቷል። ትኩረቱንም ሰዎች ከኪሳቸው ከሚያወጡት ወጪ ይልቅ፣ በጋራ ወደሚጋሩት ሳቅ እና ጨዋታ አዙሮልናል!
ነገሩ እንዲህ ነው፤ «በሳቅዎ ይክፈሉ» በሚለው አዲስ ሃሳብ፣ የሳቅፔ (SAQPay) መተግበሪያ እውነተኛ ሳቅን በመለየት ለሳቃችን ነጥብ ይሰጠናል። ተንቀሳቃሽ ስልካችን ላይ ነጥቡን እያጠራቀምን ደግሞ ሐረር ቢራን በተመረጡ ቦታዎች በቅናሽ እንድንናኝ ያስችለናል!
ሐረር ቢራ የሀገራችንን የፈጠራና የኪነጥበብ ዘርፍ የሚደግፍ ከመሆኑም በላይ፣ ሰዎች በአንድነት ተገናኝተው የሚዝናኑበት ሰፊ እድል በመፍጠር ላለፉት 40 ዓመታት ማህበረሰባችንን በሳቅና በጨዋታ ሲያገናኝ ቆይቷል። ይሄ አዲስ ሃሳብም የዚሁ የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነታችን አንዱ ማሳያ ነው!
“ለእኛ ለሐረሮች፣ ከገንዘብ ልውውጥ ይልቅ እጅግ ትርጉም ያለው ነገር አብረን የምንጋራው ደስታ እና በእውነተኛ ሳቅ ውስጥ የሚፈጠረው አብሮነት እንደሆነ እናምናለን። «በሳቅዎ ይክፈሉ» ይሄንኑ እውነት በተግባር የምናሳይበት መንገዳችን ነው። ምክንያቱም መዝናናት ለሁሉም ክፍት ሲሆን፣ ሰዎች በአንድ ላይ ከመሰባሰብ አልፈው የእርስ በርስ ትስስራቸው ይበልጥ ይጠነክራልና!” ካሳሁን ፈለቀ፣ የሃይኒከን ኢትዮጵያ የማርኬቲንግ ዳይሬክተር
ሁሉም «በሳቅዎ ይክፈሉ» ላይ የምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በተመረጡ ቦታዎች ብቻ የሚካሄዱ ሲሆን፤ ህጋዊ የእድሜ ገደብን እና ኃላፊነት የተሞላበት መጠጥ አጠቃቀም መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ ያከበሩ ናቸው።
Source: FastMereja








No comments yet.