እንግሊዝ እንደ ካናዳ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የእንግሊዝ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጥገኝነት ጠያቂዎች የካናዳ ዓይነት አዲስ “የተገደበ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ሕጋዊ” መንገዶችን ከወራት በኋላ ይፋ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

አዲሱ አሠራር ዩኒቨርሲቲዎች፣ የማኅበረሰብ ቡድኖች እና የንግድ ተቋማትን የመሳሰሉ ድርጅቶች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ለመግባት የሚያመለክቱ ስደተኞችን ስፖንሰር እንዲያደርጉ ይፈቅዳል።

ይህ አሰራር የካናዳን የጥገኝነት ሥርዓት መሠረት ያደረገ ነው።

በሕገወጥ መንገድ እየገቡ ያሉትን ስደተኞች ለመቆጣጠር ጥረት በሚደረግበት ጊዜ አዲስ አሠራር መጀመሩን በተመለከተ፤ የወግ አጥባቂ ፓርቲ አባላት ሕገወጥ ስደት እስኪቆም ድረስ ተጨማሪ ሰዎች ወደ አገሪቱ መግባት የለባቸውም በማለት እየተከራከሩ ነው።

የዩኬ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ሻባና ማህሙድ እንደተናገሩት አዲሱ ሥርዓት “ሀቀኛ ስደተኞችን” የሚጠብቅ ሲሆን፣ “ብዙ ጊዜ አላግባብ ጥቅም ላይ የሚውሉ ክፍተቶችን ደግሞ የሚዘጋ” ነው።

ሚኒስትሯ “ብሪታንያ ሁልጊዜም ከጦርነት እና ከስደት ለሚሸሹ ሰዎች መጠጊያ ትሰጣለች።

ነገር ግን ይህ ሥርዓት የሚቆየው ሕዝቡ ፍትሐዊ፣ ቁጥጥር እንደሚደረግበት እና አላግባብ ጥቅም ላይ ለመዋል ክፍት እንዳልሆነ ካመነ ብቻ ነው” ብለዋል።

አዲሱ አሠራርን በተመለከተ ዜናው የተሰማው የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሯ የኢሚግሬሽን ረቂቅ ሕግን ለታችኛው ምክር ቤት ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ባሉበት ጊዜ ሲሆን አንዳንድ የሌበር ፓርቲ አባላት ሊቃወሙት ይችላሉ እየተባለ ነው።

በዩኬ ውስጥ በአገሪቱ ስደተኞችን መልሶ በማስፈር መርሃ ግብር ስር ስፖንሰር የሚደረጉ በአንጻራዊ ሁኔታ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ይገኛሉ።

“አብዛኞቹ” ስደተኞች ግን በአካባቢ ምክር ቤቶች ድጋፍ የተደረገላቸው መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

መንግሥት በግብር ከፋዮች ወጪ በሆቴሎች ውስጥ የሚቀመጡ ስደተኞችን ቁጥር እንዲቀንስ ጫና ሲደረግበት የቆየ ሲሆን፣ አሁንም ስደተኞች በሕገወጥ መንገድ በትናንሽ ጀልባዎች ወደ አገሪቱ መምጣት መቀጠላቸው ሕዝቡ የጥገኝነት ሥርዓቱን እንዲጠራጠር አድርጎታል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

#Britain #Canada #Emigrants
#BBC #News
#ጌጡተመስገንሚዲያናኮሚኒኬሽን
#Getutemesgen
#Mediacommunication


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: